የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ምክርቤት የተለያዩ የካቢኔ አባላት ሹመት አፀደቀ - ኢዜአ አማርኛ
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ምክርቤት የተለያዩ የካቢኔ አባላት ሹመት አፀደቀ
ታርጫ፤ መስከረም 22/2019 (ኢዜአ )፡-የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ምክር ቤት የክልሉ ርዕሰመሠተዳድር አቶ ፍቅሬ አማን ያቀረቡትን የክልሉን የስራ አስፈፃሚ አካላትን ሹመት ተቀብሎ አፅድቋል።
በዚህም መሠረት
1. ወ/ሮ ሕይወት አሰግድ፦ የክልሉ ንግድና ኢንቨስት መንግ ቢሮ ኃላፊ
2. አቶ የሺዋስ ዓለሙ፦የገቢዎች ቢሮ ኃላፊ
3. ኢንጂነር በየነ በላቸዉ፦ የክልሉ ዉሃ፣ ማዕድንና ኢነርጂ ቢሮ ኃላፊ
4. አቶ እንዳሻዉ ከበደ፦ የክልሉ ፐብሊክ ሰርቪስና የሰዉ ሀብት ልማት ቢሮ ኃላፊ
5. አቶ ፋንታሁን ብላቴ፦ የክልሉ ስራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ
6. አቶ ሰለሞን ካሳሁን፦ የክልሉ ባህል፣ ቱሪዝምና ስፖርት ቢሮ ኃላፊ
7. ወ/ሮ ሀሲያ አሊ፦ የክልሉ የመንግስት ኮሚኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ
8. አቶ ሀብታሙ ካፍቴን፦ የክልሉ ደን፣አካባቢ ጥበቃና አየር ንብረት ለዉጥ ቁጥጥር ቢሮ ኃላፊ
9. አቶ ሙሉጌታ ወ/ሚካኤል፦ የክልሉ ጤና ቢሮ ኃላፊ
10. አቶ በድሉ መዓዛ፦ የክልሉ ቆላማና አርብቶ አደር ቢሮ ኃላፊ
11. አቶ ዘመድኩን ሰለሞን፦ የክልሉ ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ቢሮ ኃላፊ
12. አቶ በላይ ተሰማ፦ የክልሉ ከተማልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ ኃላፊ
13. አቶ አንድነት አሸናፊ፦ የክልሉ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ
14. አቶ ተመስገን ከበደ፦ የክልሉ ፋይናንስ ቢሮ ኃላፊ
15. ወ/ሮ አሰለፈች መብራቱ፦ የክልሉ ሴቶችና ማህበራዊ ጉዳዮች ቢሮ ኃላፊ
16. አቶ ፌልታሞ ዲብሎ ፦ የክልሉ መንገድ ልማትና ትራንስፖርት ቢሮ ኃላፊ
17. ወ/ሮ ቤተልሔም ዳንኤል፦ የክልሉ ፍትሕ ቢሮ ኃላፊ
ተሿሚዎቹ በምክር ቤቱ ፊት ቀርበዉ ቃለመሃላ ፈፀመዋል