ዶክተር መሳይ ሀይሉ አዲሱ የሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሆነው ተሾሙ - ኢዜአ አማርኛ
ዶክተር መሳይ ሀይሉ አዲሱ የሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሆነው ተሾሙ
ሀዋሳ፤መስከረም 21/2019 (ኢዜአ) ፦ የሲዳማ ክልል ምክር ቤት ዶክተር መሳይ ሀይሉን አዲሱ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አድርጎ ሾመ።
ትልቅ ሀገር፤ ትልቅ ሕዝብ ፤ ታላቅ ርዕይ
የክልሉ ምክር ቤት መስራች ጉባዔ በሀዋሳ እየተካሄደ ይገኛል።
በዚህም ዶክተር መሳይ ሀይሉ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ሆነው ተሹመዋል።
ዶክተር መሳይ ቀደም ሲል የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ሆነው ሲያገለግሉ ነበር።
ዶክተር መሳይን ለርዕሰ መስተዳድርነት ዕጩ አድርገው ያቀረቡት በብልጽግና ፓርቲ የሲዳማ ክልል ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት ሃላፊ አቶ መምሩ ሞኬ ናቸው።
አቶ መምሩ ዶክተር መሳይን ለርዕሰ መስተዳድርነት ዕጩ ሲያቀርቡ እንዳሉት፤ ዶክተር መሳይ በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ምክትል ፕሬዝዳንትነትን ጨምሮ በተለያዩ ቦታዎች የሥራ ሃላፊ ሆነው በውጤታማነት ማገልገላቸው አንስተዋል።
ምክር ቤቱም ሹመቱን ተቀብሎ አፅድቋል።
በምክር ቤቱ ርዕሰ መስተዳድር ሆነው የተሾሙት ዶክተር መሳይ በምክር ቤት ፊት ቃለ መሃላ ፈጽመዋል።
ምክር ቤቱ በመሥራች ጉባኤው የክልሉን ምክትል ርእሰ መሥተዳድር እና ሌሎች ሹመቶችንም እንደሚያጸድቅ ይጠበቃል።