የኢትዮጵያ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን 16 ጎሎችን በማስቆጠር ሲሸልስን አሸነፈ - ኢዜአ አማርኛ
የኢትዮጵያ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን 16 ጎሎችን በማስቆጠር ሲሸልስን አሸነፈ
አዲስ አበባ ፤መስከረም 20/2019 (ኢዜአ) ፦ የኢትዮጵያ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን ከሲሸልስ ጋር ባደረገው ዓለም አቀፍ የወዳጅነት ጨዋታ ሲሸልስን 16 ለ 0 በሆነ ሰፊ የግብ ልዩነት ረትቷል።
በአበበ ቢቂላ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ንግሥት በቀለ፣ ታሪኳ ዴቢሶ፣ እሙሽ ዳንኤል፣ አረጋሽ ካልሳ እና ቤተልሄም መንተሎ በተመሳሳይ ሁለት ሁለት ግቦችን አስቆጥረዋል።
ምኅረት አየለ፣ እፀገነት ግርማ፣ ቱሪስት ለማ፣ ሚለን ጋይም፣ ዳግማዊት ሰለሞን እና ማህሌት ምትኩ ቀሪዎቹን ጎሎች ከመረብ ላይ አሳርፈዋል።
የሀገራቱ ሁለተኛ የወዳጅነት ጨዋታ ቅዳሜ መስከረም 23 ቀን 2019 ዓ.ም ይካሄዳል።
ቻለው ለሜቻ በሁለት ዓመት ውል የብሔራዊ ቡድኑ አሰልጣኝ ሆነው ባለፈው ሳምንት መሾማቸው የሚታወስ ነው።
ኢትዮጵያ ከሩዋንዳ ጋር የሁለተኛ ዙር የማጣሪያ ጨዋታዎቿን መስከረም መጨረሻ እና ጥቅምት ወር መግቢያ ላይ ታደርጋለች።
የወዳጅነት ጨዋታዎች የብሔራዊ ቡድኑ የማጣሪያ ዝግጅት አካል ናቸው።