ቀጥታ፡

‎የአፍሪካን የወደፊት እጣ ፈንታ በጋራ ልንገነባው የተገባ ኃላፊነታችን ነው

አዲስ አበባ ፤መስከረም 20/2019 (ኢዜአ) ፦ ‎የአፍሪካን የወደፊት እጣ ፈንታ በጋራ ልንገነባው የተገባ ኃላፊነታችን ነው ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልእክት፦የላሙ የነዳጅ ማጣሪያ ፋብሪካ የመሰረተ ድንጋይ የማስቀመጥ ስነሥርዓት፤ የአፍሪካን የኢንዱስትሪ አቅም ለማሳደግ፣ መጠነ ሰፊ እድሎችን ለመፍጠር እና በመላው ምስራቅ አፍሪካ ለላቀ ኢኮኖሚያዊና የኢንዱስትሪ ሉዓላዊነትን መሰረት ለመጣል ትልቅ እርምጃ መሆኑን የሚያረጋግጥ ሁነት መሆኑን ገልጸዋል።

‎

‎በአህጉራችን የምትገኙ የኢንዱስትሪ መሪዎች፣ ባለሀብቶች እና ስራ ፈጣሪዎች፤ በአፍሪካ ላይ ኢንቨስት ልታደርጉ፣ ባለን አቅምና የጋራ ጸጋ እምነት ሊኖራችሁ እንዲሁም አህጉራዊ መፃኢ እድላችንን የሚወስኑ ለውጥ አምጪ ፕሮጀክቶችን ልትገነቡ ይገባል ሲሉም ጥሪ አቅርበዋል።

‎‎የአፍሪካን የወደፊት እጣ ፈንታ በጋራ ልንገነባው የተገባ ኃላፊነታችን ነውም ብለዋል፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም