ቀጥታ፡

አቶ ሳሙኤል ሞላልኝ የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ እና የፕላን ልማት ቢሮ ኃላፊ ሆነው ተሾሙ

አዲስ አበባ፤ መስከረም 20/2019 (ኢዜአ)፦ የአዲስ አበባ ምክር ቤት አቶ ሳሙኤል ሞላልኝን የከተማዋ ምክትል ከንቲባ እና የፕላን ልማት ቢሮ ኃላፊ አድርጎ ሾሟል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት የመንግሥት ምስረታና የ4ኛ ዙር የመክፈቻ ጉባኤ እያካሄደ ይገኛል።

አቶ ሳሙኤል ሞላልኝ ቀደም ሲል የደሴ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ የነበሩ ሲሆን በተለያዩ የስራ ኃላፊነቶችም አገልግለዋል፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም