ቀጥታ፡

ትናንት ያየነው ለውጥ መዳረሻችን ሳይሆን የቀጣዩ ጉዟችን መነሻ ነው -ከንቲባ አዳነች አቤቤ

አዲስ አበባ፤ መስከረም 20/2019 (ኢዜአ)፦ ትናንት ያየነው ለውጥ መዳረሻችን ሳይሆን የቀጣዩ ጉዟችን መነሻ ነው ሲሉ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ።

የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት የከተማ አስተዳደር መንግሥት ምስረታና 4ኛ ዙር የመክፈቻ ጉባዔውን እያካሄደ ይገኛል።


 

ምክር ቤቱ በጉባኤው አዳነች አቤቤን የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አድርጎ መርጧል፡፡

ከንቲባዋ በዚሁ ወቅት ባደረጉት ንግግር፣ ዛሬ የምንቀበለው ሹመትን ብቻ ሳይሆን የህዝብ አደራ ጭምር ነው ብለዋል።

"ያለፉትን አምስት አመት የከተማችንን መልክ እንቀይራለን፣ ብለን ቃል ገብተን ነበር ይህም ከጠበቅነውና ካቀድንው በላይ ተሳክቶልናል" ነው ያሉት።

ነገር ግን የትናንቱ ስኬት የነገ ኃላፊነትን አይተካም፤ በቀጣይ የነዋሪዎቻችንን ኑሮ በተጨባጭ ማሻሻል የሚችሉ ስራዎችን ማከናወን ይጠበቅብናል ብለዋል፡፡

የአገልግሎት አሰጣጠን ዲጂታላይዝ በማድረግ ነዋሪዎችን ከእንግልትና ከቢሮክራሲ ውጣ ውረድ ለመታደግ በትኩረት እንሰራለን ብለዋል።

ትናንት ያየነው ለውጥ መዳረሻችን ሳይሆን የቀጣዩ ጉዟችን መነሻ ነው ሲሉም ነው የገለጹት።

በዚህም ከተማዋን እውነተኛ የብልጽግና ማዕከል ለማድረግ የተያዘው ራዕይ እውን እንደሚሆን አብራርተዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም