ቀጥታ፡

የዋሊያዎቹ ደጋፊዎች በባህር ዳር ዓለም አቀፍ ስታዲየም ለሚካሄደው የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ለድጋፍ ተዘጋጅተዋል

ባሕርዳር፤ መስከረም 19/ 2019 (ኢዜአ)፡-የዋሊያዎቹ ደጋፊዎች በባህር ዳር ዓለም አቀፍ ስታዲየም ለሚካሄደው የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ለድጋፍ ተዘጋጅተዋል።

በኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን (ዋሊያዎቹ) ከሴኔጋል ብሄራዊ ቡድን ጋር ለሚያደርጉት ጨዋታ ደጋፊዎች የብሄራዊ ቡዱኑን ማሊያና ሰንደቅ አላማ ለብሰው ቡድናቸውን ለማበረታታት ስታዲየም እየገቡ ነው።


 

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን (ዋሊያዎቹ) እና የሴኔጋል ብሔራዊ ቡድን ወሳኝ የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታ ለመታደም የዋልያዎቹ ደጋፊዎች በጉጉት እየተጠባበቁ ነው። 

ከባህር ዳር ከተማ በሁሉም አቅጣጫዎች ደጋፊዎች በሰንደቅ ታጅበውና ሀገር ፍቅር ስሜት ተሞልተው ለድጋፍ እየተመሙ ይገኛሉ።

 ስታዲየሙ የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን (ካፍ) እና የዓለም አቀፍ የእግር ኳስ ማህበራት ፌዴሬሽን (ፊፋ) ያስቀመጧቸውን መስፈርቶች መሠረት አድርጎ መገንባቱ የሚታወቅ ነው።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም