ቀጥታ፡

የኢትዮጵያ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን ከሲሸልስ ጋር የወዳጅነት ጨዋታ ያደርጋል

አዲስ አበባ፤ መስከረም 18/2019 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን ከሲሸልስ ጋር ዓለም አቀፍ የወዳጅነት ጨዋታ እንደሚያከናውን የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አስታወቀ።

ብሔራዊ ቡድኑ በ2028 ኦሊምፒክ ሴቶች እግር ኳስ ማጣርያ ከሩዋንዳ ጋር ለሚያደርጉት ጨዋታ ዝግጅት ላይ ይገኛሉ።

በለሜቻ ግርማ የሚሰለጥነው ቡድኑ ከሲሸልስ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን ጋር ሁለት ዓለምአቀፍ የወዳጅነት ጨዋታዎች ያደርጋሉ።

የመጀመርያው ጨዋታ ረቡዕ መስከረም 20፣ ሁለተኛው ጨዋታ ቅዳሜ መስከረም 23 በተመሳሳይ በአበበ በቂላ ስታዲየም ከቀኑ ዘጠኝ ሰዓት ላይ እንደሚካሄድ ፌዴሬሽኑ አመልክቷል።

በሁለት ዓመት ውል የብሔራዊ ቡድኑ አሰልጣኝ ሆነው ባለፈው ሳምንት የተሾሙት ቻለው ለሜቻ ለ34 ተጫዋቾች ጥሪ አድርገው ዝግጅት እያደረጉ ይገኛል።

ኢትዮጵያ ከሩዋንዳ ጋር የማጣሪያ ጨዋታዎቿን መስከረም መጨረሻ እና ጥቅምት ወር መግቢያ ላይ ታደርጋለች።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም