ቀጥታ፡

ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በበርሊን ማራቶን በሁለቱም ጾታዎች አሸነፉ

አዲስ አበባ፤ መስከረም 17/2019 (ኢዜአ)፦  52ኛው የበርሊን ማራቶን ዛሬ ረፋድ ላይ ተካሄዷል።

በሴቶች አትሌት ትዕግስት አሰፋ በ2 ሰዓት ከ11 ደቂቃ ከ04 ሴኮንድ አሸንፋለች።

አትሌቷ እስከ 40ኛው ኪሎ ሜትር የዓለም ክብረ ወሰንን ለመስበር በሚያስችል ፍጥነት እየሮጠች የነበረች ቢሆንም ባጋጠማት መጠነኛ ጉዳት እቅዷ ሳይሳካ ቀርቷል።

የመጨረሻዎቹን ሁለት ኪሎ ሜትሮች በጽናት የጨረስችበት መንገድ አድናቆት አስችሯታል።

አትሌቷ የበርሊን ማራቶንን ስታሸንፍ የአሁኑ ለሶስተኛ ጊዜ ነው።

የሴቶች ማራቶን የዓለም ክብረ ወሰን በኬንያዊቷ አትሌት ሩት ቼፕጌቲች በ2 ሰዓት ከ9 ደቂቃ ከ56 ሴኮንድ የተያዘ ነው።

በዳቱ ሂርጳ 2 ሰዓት ከ16 ደቂቃ ከ53 ሴኮንድ ሁለተኛ ስትወጣ ደራ ዲዳ 2 ሰዓት ከ16 ደቂቃ ከ55 ሴኮንድ ሶስተኛ ደረጃን ይዛ አጠናቃለች።




በወንዶች አትሌት ጉዬ አዶላ 2 ሰዓት ከ2 ደቂቃ ከ50 ሴኮንድ አሸናፊ ሆኗል።

ሌላኛው ኢትዮጵያዊ አትሌት ገመቹ ዲዳ 2 ሰዓት ከ3 ደቂቃ ከ19 ሴኮንድ ሁለተኛ ወጥቷል።

ታንዛንያዊው አትሌት ጋብርኤል ጌራልድ ጋይ በ2 ሰዓት ከ3 ደቂቃ ከ59 ሴኮንድ ሶስተኛ ደረጃን ይዞ አጠናቋል።

ከዚህ ቀደም ከአምስት ዓመት በፊት ውድድሩን አሸንፏል።

አትሌቱ በባለፈው ዓመት ውድድር አራተኛ ሆኖ ማጠናቀቁ የሚታወስ ነው።

እ.አ.አ በ1974 የተጀመረው የበርሊን ማራቶን በዓለም ላይ ከሚታወቁ ትላልቅ የማራቶን ውድድሮች መካከል አንዱ ነው።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም