የመስቀል በዓል በመላ ሀገሪቱ እየተከበረ ነው - ኢዜአ አማርኛ
የመስቀል በዓል በመላ ሀገሪቱ እየተከበረ ነው
አዲስ አበባ፤ መስከረም 17 /2019 (ኢዜአ)፡- የመስቀል በዓል በክርስትና እምነት ተከታዮች ዘንድ በመላ ሀገሪቱ እየተከበረ ነው::
በዓሉ በተለያዩ ሐይማኖታዊ እና ባህላዊ ሥነ ሥርዓቶች ነው በድምቀት እየተከበረ የሚገኘው።
በትናንትናው ዕለት የመስቀል ደመራ በዓል በአዲስ አበባ መስቀል አደባባይ በደማቅ ሥነ-ሥርዓት መከበሩ ይታወሳል።
በሥነ ሥርዓቱ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማቲያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት፣ የሕንድ ማላንካራ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ ባስልዮስ ማርቶማ ማቴዎስ ሣልሳዊ፣ የአዲስ አበባ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ፣የባህል እና ስፖርት ሚኒስትር ሸዊት ሻንካ፣ ብፁዓን አባቶች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ ከፍተኛ የመንግሥት የስራ ኃላፊዎች፣ ዲፕሎማቶች ታድመዋል።
በአዲስ አበባ የሚገኙ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ-ክርስቲያንና አድባራት የሰንበት ትምህርት ቤት መዘምራንና ሊቃውንት ኃይማኖታዊ ኅብረ ዝማሬን አቅርበዋል።
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ-ክርስቲያን ፓትርያርክ ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ በትናንትናው ዕለት በመስቀል ደመራ በዓል ላይ ባስተላለፉት መልዕክት፥ ኢትዮጵያውያን ለሀገራቸው ዘላቂ ሰላምና አንድነት መረጋገጥ አበክረው ሊሰሩ ይገባል ብለዋል፡፡