ቀጥታ፡

የመስቀል ደመራ በዓል የሰላምና የፍቅር እንዲሁም የብርሃንና የብሩህ ተስፋ ስንቅ ነው

ሎጊያ፣መሰከረም 16/2019(ኢዜአ) ፡-የመስቀል ደመራ በዓል የሰላምና የፍቅር እንዲሁም የብርሃንና የብሩህ ተስፋ ስንቅ መሆኑን በኢትዮጵያ  ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የአፋር ሀገረ ስብከት የቁጥጥር ኀላፊ ርዕሰ ደብር መርጌታ ሰለሞን ሐይሌ ተናገሩ።

የመሰቀል ደመራ በዓል በሎጊያ ከተማ በተለያዩ ሐይማኖታዊ  ሰነ ሰርዓት ታጅቦ በድምቀት ተከብሯል።


 

በበዓሉ የተገኙት በኢትዮጵያ  ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የአፋር ሀገረ ስብከት የቁጥጥር ኀላፊ ርዕሰ ደብር መርጌታ ሰለሞን ሐይሌ፤ የመስቀል ደመራ በዓል የሰላምና የፍቅር እንዲሁም የብርሃንና የብሩህ ተስፋ ስንቅ መሆኑን ገልጸዋል።

በመሆኑም በዓሉ ሲከበር ይህንን እሴቱን በመሰነቅ ሰላምን፣ አብሮነትና መተጋገዝን መሰረት በማድረግ መሆኑን ተናግረዋል።


 

ኢዜአ ያነጋገራቸው የበዓሉ ታዳሚዎችም የመስቀል ደመራ በዓልን በፍቅር፣ አብሮነትና በመጠያየቅ የሚያከብሩት መሆኑን ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም