ቀጥታ፡

የመስቀል ደመራ በዓል በመስቀል አደባባይ በድምቀት ተከበረ

አዲስ አበባ፤ መስከረም 16/2019 (ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ-ክርስቲያን በአደባባይ በድምቀት የሚከበረው የመስቀል ደመራ በዓል በአዲስ አበባ መስቀል አደባባይ በደማቅ ሥነ-ሥርዓት ተከብሯል።

በሥነ ሥርዓቱ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማቲያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት፣ የሕንድ ማላንካራ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ ባስልዮስ ማርቶማ ማቴዎስ ሣልሳዊ፣ የአዲስ አበባ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ፣የባህል እና ስፖርት ሚኒስትር ሸዊት ሻንካ፣ ብፁዓን አባቶች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ ከፍተኛ የመንግሥት የስራ ኃላፊዎች፣ ዲፕሎማቶች ታድመዋል።

በአዲስ አበባ የሚገኙ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ-ክርስቲያንና አድባራት የሰንበት ትምህርት ቤት መዘምራንና ሊቃውንት ኃይማኖታዊ ኅብረ ዝማሬን አቅርበዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም