የመስቀል ደመራ በዓል በኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን እየተከበረ ይገኛል - ኢዜአ አማርኛ
የመስቀል ደመራ በዓል በኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን እየተከበረ ይገኛል
አዲስ አበባ፤ መስከረም 16/2019 (ኢዜአ)፦ የመስቀል ደመራ በዓል በኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን እየተከበረ ይገኛል
የመስቀል ደመራ በዓል በኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን በአዲስ አበባ ጽዮን ማርያም ቤተ-ክርስቲያን እየተከበረ ይገኛል።
በበዓሉ አከባበር ሥነ-ሥርዓት ላይ የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተ-ክርስቲያን አባቶችና የእምነቱ ተከታዮች ታድመዋል።
የደመራ በዓሉ በጸሎት ፕሮግራም እንዲሁም የተለያዩ ዝማሬዎች በድምቀት እየተከበረ ይገኛል።
የመስቀል ደመራ በዓል እ.አ.አ በ2013 በተባበሩት መንግሥታት የትምህርት፣ የሳይንስና የባህል ድርጅት (ዩኔስኮ) የዓለም ቅርስ ሆኖ መመዝገቡ ይታወሳል።