የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ሽንፈት አስተናገደ - ኢዜአ አማርኛ
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ሽንፈት አስተናገደ
አዲስ አበባ፤ መስከረም 15/2019 (ኢዜአ)፦ በ36ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ የመጀመሪያ ጨዋታውን ያደረገው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በሱዳን 1 ለ 0 ተሸንፏል።
በጁባ ብሔራዊ ስታዲየም በተካሄደው የምድብ 10 ጨዋታ መሐመድ ማሙን በ86ኛው ደቂቃ ግቧን በፍጹም ቅጣት ምት አስቆጥሯል።
በአሰልጣኝ ዮሐንስ ሳህሌ የሚመራው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ሁለተኛ የምድብ ጨዋታውን ማክሰኞ መስከረም 19 ቀን 2019 ዓ.ም ከሴኔጋል ጋር በባህር ዳር ስታዲየም ያከናወናል።
ሱዳን ከሞዛምቢክ በተመሳሳይ መስከረም 19 ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።
በዚሁ ምድብ ዛሬ በተመሳሳይ ሰዓት በተደረገ ሌላኛው ጨዋታ ሴኔጋል እና ሞዛምቢክ አንድ አቻ ተለያይተዋል።