ቀጥታ፡

ለመስቀል በዓል በቂ የእርድ እንስሳት አቅርቦት በመኖሩ በተረጋጋ ሁኔታ እየተገበያየን ነው- ሸማቾችና ነጋዴዎች

ቢሻን ጉራቻ፤ መስከረም 15/2019 (ኢዜአ) ፦በቢሻን ጉራቻ ከተማ ለመስቀል በዓል በቂ የእርድ እንስሳት አቅርቦት በመኖሩ በተረጋጋ ሁኔታ እየተገበያዩ መሆናቸውን ሸማቾችና ነጋዴዎች ገለጹ።

በክርስትና እምነት ተከታዮች ዘንድ ከሚከበሩ ሀይማኖታዊ በዓላት መካከል አንዱ የሆነው የመስቀል በዓል መስከረም 17 ቀን 2019 ዓ.ም ይከበራል።

የበዓል የእርድ እንስሳት ግብይት ከሚካሄድባቸው አካባቢዎች መካከል ደግሞ የቢሻን ጉራቻ የቁም እንስሳት ገበያ ተጠቃሽ ነው።

የበዓል ገበያውን አስመልክተው ለኢዜአ አስተያየታቸውን የሰጡ ሸማቾችና ነጋዴዎች፤ በከተማው ለመስቀል በዓል በቂ የእርድ እንስሳት አቅርቦት በመኖሩ በተረጋጋ ሁኔታ እየተገበያዩ መሆኑን ገልጸዋል።


 

አስተያየታቸውን ከሰጡ የእርድ ከብት ሲገዙ ያገኘናቸው አቶ ሀይለኢየሱስ ሻንካ እና አቶ በለጠ አሰፋ የመስቀል በዓል ገበያው ካለፉት በዓላት አንጻር በዋጋም ሆነ በአቅርቦት የተሻለ ነው ብለዋል።


 

 አርሶ አደሩም እንስሳትን በአግባቡ አደልቦ ለገበያ በማቅረብ ተጠቃሚ ለመሆን እንዳስቻለውም ገልጸዋል።


 

የእርድ ሰንጋ ነጋዴ የሆኑት አቶ ከድር ሁሴን በበኩላቸው፤ በበዓል ገበያው ሸማቹ እንደ አቅሙ ገዝቶ ለመጠቀም የሚያስችል አቅርቦት መኖሩን ጠቅሰው ግብይቱም  የተረጋጋ መሆኑን ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም