በአዲስ አበባ ከተማ ለመስቀል ደመራ በዓል የሚዘጉ መንገዶችን ይፋ አደረገ - ኢዜአ አማርኛ
በአዲስ አበባ ከተማ ለመስቀል ደመራ በዓል የሚዘጉ መንገዶችን ይፋ አደረገ
አዲስ አበባ፤ መስከረም 15/2019 (ኢዜአ)፦ በአዲስ አበባ ከተማ ለመስቀል ደመራ በዓል ከዋዜማው ጀምሮ ለተሽከርካሪዎች ዝግ የሚሆኑ መንገዶችን የከተማ አስተዳደሩ ፖሊስ ይፋ አድርጓል፡፡
በከተማው ከዛሬ ከቀኑ 5 ሰዓት ጀምሮ እስከ መርሃ ግብሩ ፍጻሜ የሚዘጉት መንገዶች የሚከተሉት ናቸው፦
• ከ 22 ማዞሪያ ወደ መስቀል አደባባይ ቅዱስ ዑራኤል አደባባይ ላይ እና ታች
• ከቦሌ ኤርፖርት ወደ መስቀል አደባባይ ደንበል ወይም ኦሎምፒያ ላይ እና ታች
• ከጎፋ ፣ በታቦት ማደሪያ ወደ ለገሃር መብራት ቂርቆስ ቤ/ክርስቲያን መስቀለኛ
• ከሜክሲኮ አደባባይ ወደ መሰቀል አደባባይ ለገሃር መብራት
• ከለገሃር ቴሌ ወደ ስታዲየም ንግድ ባንክ ክቡ ህንጻ መስቀለኛ
• ከቸርቸል ጎዳና ፣ በአምባሳደር ወደ መስቀል አደባባይ ሐራምቤ መብራት ላይ
• ከአራት ኪሎ ፣ በውጭ ጉዳይ ሚ/ር ወደ መስቀል አደባባይ ብሔራዊ ቤተ መንግሥት መስቀለኛ
• ከካዛንቺስ መብራት ወደ መስቀለኛ መቅረዝ ሆስፒታል የሚወስዱ መንገዶች ለተሽከርካሪ ዝግ በመሆናቸው አሽከርካሪዎች አማራጭ መንገዶችን እንዲጠቀሙ ፖሊስ አስታውቋል።
ነገ ከንጋቱ 12 ሰዓት ጀምሮ በተገለፁት መንገዶች ላይ ለአጭርም ሆነ ለረጅም ጊዜ ተሽከርካሪ አቁሞ መሄድ መከልከሉንም አመልክቷል።
ህብረተሰቡ የፖሊስን አገልግሎት ለማግኘትም ሆነ ጥቆማ ለመስጠት በ0111-11-01-11 እና በ990 ነፃ የስልክ መስመር መጠቀም እንደሚቻልም ተጠቁሟል።