ቀጥታ፡

የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የመጀመሪያ ዙር መርሃ ግብር ይፋ ሆነ

አዲስ አበባ፤ መስከረም 15/2019 (ኢዜአ)፦ የ2019 የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የመጀመሪያ ዙር መርሐ ግብር የሚካሄድባቸው ቀናት እና ቦታዎች ይፋ ሆነዋል።

የፕሪሚየር ሊግ የዕጣ ማውጣት መርሃ ግብር መስከረም 10/ 2019 ዓ.ም መከናወኑ የሚታወስ ነው።

አሁን ደግሞ የመጫወቻ ቦታዎችን፣ ቀናትን እና ሰዓቶችን ያካተተው ሙሉ የመጀመሪያ ዙር መርሃ ግብር ይፋ መደረጉን የሊጉ አክሲዮን ማህበር አስታውቋል።

ፕሪሚየር ሊጉ መስከረም 29 2019 ዓ.ም የሚጀመር ሲሆን ጥር 9 2019 ዓ.ም የመጀመሪያ ዙር ይጠናቀቃል።

አህጉር አቀፍ ጨዋታ ያለባቸው ሲዳማ ቡና እና ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ የሁለተኛ፣ የሶስተኛ እና የአራተኛ ሳምንት ጨዋታዎች በተስተካካይ መርሃ ግብር እንደሚደረጉ ማህበሩ ገልጿል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም