አዲስ አበባ፣ ኦሮሚያ እና ድሬዳዋ በሀገር አቀፍ የውሃ ዋና ውድድር አሸናፊ ሆኑ - ኢዜአ አማርኛ
አዲስ አበባ፣ ኦሮሚያ እና ድሬዳዋ በሀገር አቀፍ የውሃ ዋና ውድድር አሸናፊ ሆኑ
አዲስ አበባ፤ መስከረም 15/2019 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ውሃ ዋና ስፖርቶች ፌዴሬሽን ያዘጋጀው የ2019 ክልሎች እና ክለቦች የውሃ ዋና ውድድር ፍጻሜውን አግኝቷል።
ውድድሩ በጋምቤላ ክልል ከመስከረም 10 እስከ 14 ቀን 2019 ዓ.ም በሁለቱም ጾታዎች ተካሄዷል።
ተተኪ ስፖርተኞችን ማፍራት እና በዓለም አቀፍ ደረጃ በሚካሄዱ ውድድሮች ላይ ሀገራቸውን የሚወክሉ ስፖርተኞችን መምረጥ ዓላማ በማድረግ ውድድሩ ተከናውኗል።
በውድድሩ አዲስ አበባ፣ ኦሮሚያ፣ ድሬዳዋ፣ጋምቤላ፣ ኦሮሚያ ፖሊስ፣ ሮቤል ክለብ፣ ላፍቶ ክለብ እና ጊዮን ሆቴል ተሳትፈዋል።
በአዋቂ ምድብ በተካሄደው ውድድር አዲስ አበባ በሴቶች 17፣ በወንዶች ደግሞ 11 የወርቅ ሜዳሊያዎችን በማስመዝገብ ውድድሩን በበላይነት አጠናቋል።
በታዳጊ ሴቶች ምድብ ኦሮሚያ በበላይነት ሲያጠናቅቅ በወንዶች ድሬዳዋ አሸናፊ ሆኗል።
ጋምቤላ ክልል ልዩ የዋንጫ ተሸላሚ በመሆን ውድድሩን ማጠናቀቁን የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር በመረጃ ያመለክታል።