ቀጥታ፡

ተቋሙ የቴክኖሎጂ ፈጣሪዎችንና ራሳቸውን የቻሉ ኢንተርፕሩነሮችን በማፍራት ረገድ የበኩሉን ሚና እየተወጣ ይገኛል

‎አዲስ አበባ፣መስከረም 15/2019 (ኢዜአ)፦የኢፌዲሪ ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት የቴክኖሎጂ ፈጣሪዎችንና ራሳቸውን የቻሉ ኢንተርፕሩነሮችን በማፍራት ረገድ የበኩሉን ሚና እየተወጣ መሆኑን ገለጸ።

ተቋሙ የሥራ እንቅስቃሴዎቹን ለህብረተሰቡ ለማስተዋወቅ የሚያስችለውንና ለ15 ቀናት የሚቆየውን 'የመረጃ ሳምንት' በተመለከተ መግለጫ ሰጥቷል።


 

‎‎የኢንስቲትዩቱ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ሀብታሙ ሙሉጌታ (ዶ/ር) በዚሁ ወቅት፤ በተቋሙ ውስጥ የተደራጁ ዎርክሾፖች፣ ላቦራቶሪዎች እና የመለማመጃ ቦታዎች መኖራቸው ለወጣቶች ትልቅ አቅም እና ዕድል እንደሚፈጥር ገልጸዋል።

ተቋሙ ወጣቶች ስራ ለመፍጠር የሚያስችላቸው ትልቅ ዕድል እንዳስገኘ ጠቅሰዋል።

በዚህ መሰረት ተቋሙ ሀገሪቱን ሊለውጡ የሚችሉ ቴክኖሎጂ ፈጣሪዎችንና ራሳቸውን የቻሉ ኢንተርፕሩነሮችን በማፍራት ረገድ የበኩሉን ሚና እየተወጣ እንደሚገኝ ገልጸዋል።

በ2019 ዓ.ም የሚቀበላቸውን ተማሪዎች ውጤታማ  ትምህርት ለመስጠት በቂ ዝግጅት ማድረጉንም ተናግረዋል።

ባለፉት ሁለት ዓመታት ብቻ የዘመኑን ፍላጎት የዋጁ ወደ 11 የሚጠጉ አዳዲስ ፕሮግራሞች መጀመራቸውን አስታውቀዋል።

ከእነዚህ መካከል የሰው ሰራሽ አስተውሎት(ኤአይ) ስልጠና ፕሮግራም አንዱ ሲሆን፣ በዚሁ መርሀ ግብር ከ2018 ዓ.ም ጀምሮ ተማሪዎችን ተቀብሎ እያሰለጠነ እንደሚገኝ ገልጸዋል።


 

የኢንስቲትዩቱ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ጸዳለ ተክሉ በበኩላቸው፣ ኢንስቲትዩቱ ለትምህርት ጥራት የሰጠው ትኩረት ተጨባጭ ውጤቶችን እያመጣ መሆኑን ገልጸዋል።

ተቋሙ የ ISO 9001:2015 እውቅናን በዋናው ካምፓስ ማረጋገጥ መቻሉን አስረድተዋል።


‎

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም