አረንጓዴ ዓሻራ፡ የመደመር እሳቤ አብነት - ኢዜአ አማርኛ
አረንጓዴ ዓሻራ፡ የመደመር እሳቤ አብነት
በሀገራችን አንዱ የማድረግ ዐቅም ማሳያ የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር ነው።የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር በዓለም በስፋት እየተስተዋለ ካለው የአየር ንብረት ግብዝነት (Greenwashing) ፍጹም ተቃራኒ በሆነ መንገድ ከንግግር ተግባርን ያስቀደመ መርሐ ግብር ዓላማው የደን ሽፋንን ማሳደግና የደን መጨፍጨፍ፣ የመሬት መራቆትና የአየር ንብረት ለውጥ ችግሮችን መፍታት የሆነው የኢትዮጵያ አረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር፤ የአካባቢ መራቆትና የአየር ንብረት ለውጥ ተግዳሮቶችን ተጨባጭ በሆኑ ተግባራት ለመፍታት መሰጠ ሰፊና የላቀ ውጤት የተመዘገበበት ተግባራዊ ጥረት ነው።
እንዲህ ያለው ትልቅ ፕሮጀክት በፌዴራል፣ በክልልና በአካባቢ ደረጃና ልዩ የሆነ የአመራር ቁርጠኝነትና ቅንጅትን ይፈልጋል። ይህ የአመራር ጥበብና ቅንጅት የተለያዩ ማኅረሰቦችን፣ ትምህርት ቤቶችን፣ የንግድ ተቋማትና ዓለም አቀፍ አጋሮችን ያሳተፈ አካታች መርሐ ግብር ነው። የአረንጓዴ ዐሻራ ፕሮግራም የጋራ የኃላፊነት ስሜትን በማጎልበት፣ ተነሣሽነቱ ከዛፍ ተከላ በላይ ሆኖ ወደ ሀገራዊ ንቅናቄ አድጓል። የተለያዩ ቡድኖች ለጋራ ዓላማ ተባብረው እንዲሠሩ አስችሏል።
የማስፈጸም ሂደቱ ዛፍ በመትከል ላይ ብቻ ያተኮረ አልነበረም። ሁሉንም ማኅበረሰብ ያሳተፈ ነበር። አካሄዱም ሊላካ የሚችል ከባቢያዊ ጥቅም የሚያስገኝ እንቅስቃሴ መፍጠር ነበር። የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር ስኬት ሀገራዊ ኩራትና ጽናት እንዲጎለብት አስችሏል። አጣዳፊ ሀገራዊና ዓለም አቀፍ ተግዳሮቶችን ለመፍታት በመደመር ስሌት ጠንካራ የአፈጻጸም ጥበብ ያለውን ዐቅምም አሳይቷል።
የመደመር መንግሥት ገጽ 127 እና 128