የኢትዮጵያ የስንዴ ምርታማነት አፍሪካ ራሷን መመገብ ትችላለች የሚል ግልጽ መልዕክት አስተላልፏል- ፕሬዝዳንት ታዬ አፅቀሥላሴ - ኢዜአ አማርኛ
የኢትዮጵያ የስንዴ ምርታማነት አፍሪካ ራሷን መመገብ ትችላለች የሚል ግልጽ መልዕክት አስተላልፏል- ፕሬዝዳንት ታዬ አፅቀሥላሴ
አዲስ አበባ፤ መስከረም 14/2019 (ኢዜአ):- የኢትዮጵያ የስንዴ ምርታማነት አፍሪካ ራሷን መመገብ ትችላለች የሚል ግልጽ መልዕክት ማስተላለፉን ፕሬዝዳንት ታዬ አፅቀሥላሴ ገለጹ።
81ኛው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ በኒው ዮርክ እየተካሄደ ይገኛል።
ፕሬዝዳንቱ ማምሻውን በጠቅላላ ጉባኤው ላይ ባደረጉት ንግግር ኢትዮጵያ በምግብ ዋስትና ዙሪያ ከፍተኛ እመርታ ማስመዝገቧን ገልጸዋል።
ኢትዮጵያ የአየር ንብረት ለውጥን የሚያቋቁም የተሻሻለ የስንዴ ዝርያ ዘር በማምረት ረገድ ስኬት ማስመዝገቧን አመልክተዋል።
በጣም በአጭር ጊዜ ውስጥ ኢትዮጵያ ከስንዴ አስመጪነት ወጥታ በአፍሪካ ካሉ ትላልቅ የስንዴ አምራቾች አንዷ መሆን መቻሏን ተናግረዋል።
የምግብ አቅርቦት የፖለቲካ አጀንዳ በሆነበት እና የዓለም የምግብ አቅርቦት ሰንሰለት በተፈተነበት በዚህ ወቅት፣ የኢትዮጵያ የስንዴ ምርታማነት አፍሪካ ራሷን መመገብ ትችላለች የሚል ግልጽ መልዕክት ማስተላለፉን ገልጸዋል።