ቀጥታ፡

የተስፋ ምህዳር - የበለጸገች ኢትዮጵያ

እንደ መግቢያ 

በአንድ ሀገር የፖለቲካ ሥርዓት ውስጥ የዜጎችን ንቁ ተሳትፎ ማረጋገጥ እጅግ አስፈላጊና መሰረታዊ ከሆኑ ጉዳዮች መካከል አንዱ ነው። ይህ ተሳትፎ አካታችነትን ባረጋገጠ የፖለቲካ ምህዳር ሲደገፍ በሀገር ውስጥ የተረጋጋ የፖለቲካ ሥርዓት ለማስፈን መሠረት ይሆናል። እንደ ኢትዮጵያ ባሉ ብዝሃ-ባህል፣ ብዝሃ-ማንነት እና የተለያዩ የፖለቲካ አመለካከቶች በሚገኙባት ሀገር ደግሞ አሳታፊ እና አካታች የፖለቲካ ሥርዓት መዘርጋት አስፈላጊነቱ ከፍተኛ ነው።

በኢትዮጵያ ባለፉት ዓመታት የፖለቲካ ሥርዓቱ አሳታፊ እና አካታች እንዲሆን በርካታ ተግባራት ተከናውነዋል። እነዚህ ተግባራት ለሀገሪቱ ዘላቂ ሰላም፣ ለዲሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ እና ለሁለንተናዊ ዕድገት ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያበረከቱ ይገኛሉ።

አካታች የፖለቲካ ስርዓት ግንባታ ጉዞ

ኢትዮጵያ እየተገበረችው የምትገኘው አሳታፊና አካታች የፖለቲካ ስርዓት የፖለቲካ ምህዳሩ እንዲሰፋ ጉልህ አስተዋጽኦ እያበረከተ ይገኛል። በዚህም ባለፉት ዓመታት የመደመር መንግስት አካታች የፖለቲካ ስርዓት ለመትከል ያለውን ቁርጠኝነት በተግባር አስመስክሯል። የተለያዩ የፖለቲካ ሀይሎች፣ የሲቪክ ማህበራት እና ግለሰቦች ሀሳባቸውን በነፃነት እንዲገልጹ ብሎም በትላልቅ ሀገራዊ ውሳኔዎች ላይ ቀጥተኛ ተሳትፎ ማድረግ እንዲችሉ በመንግስት የአስፈጻሚነት የስልጣን እርከኖች ላይ ተመድበው ሀገራቸውን እያገለገሉ ይገኛሉ።

ለዚህም ባለፉት ዓመታት የመደመር መንግስት በሚኒስትርነትና በሚኒስትር ዴኤታ እርከን የሾማቸው እንዲሁም የተለያዩ የመንግስት ተቋማትን እንዲመሩ የተመደቡ የተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲ አመራር አባላትን መመልከት በቂ ነው። ይህም  ለአሳታፊ እና አካታች የፖለቲካ ስርዓት መጎልበት ያለውን ጽኑ ፍላጎት በተግባር ካረጋገጠባቸው መስኮች መካከል ተጠቃሽ ነው።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (/) ከሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ በፊት ከተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲ ተወካዮች ጋር ባደረጉት ውይይት ወቅት አጽንኦት እንደሰጡት፤ ኢትዮጵያን በማጽናትና በማልማት ላይ ከተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር አብሮ መስራት ያስፈልጋል።

የመደመር መንግስት የፖለቲካ ምህዳሩ እንዲሰፋ ያለውን ቁርጠኝነት በተግባር ማሳየቱ እንደተጠበቀ ሆኖ ከተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር በማያግባቡ ጉዳዮች ላይ በመከራከር ኢትዮጵያን በማጽናትና በማልማት ላይ አብሮ መስራት እንደሚያስፈልግም እንዲሁ።

ለፖለቲካ ስርዓት አሳታፊነት እና አካታችነት እንደማሳያ ከሚቀርቡ ጉዳዮች መካከል በአንድ ሀገር የሚከናወን የምርጫ ሂደት ይጠቀሳል። ኢትዮጵያ ለምርጫ አሳታፊነት እና አካታችነት መረጋገጥ የሰጠችው ትኩረት 2018 . በተካሄደው ሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ የታየው የፖለቲካ ፓርቲዎችም ሆነ የህዝቡ ንቁ ተሳትፎ እንዲሁም የተመዘገበው ውጤት ጥሩ ማሳያ ነው

ሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ከመጀመሪያው ጀምሮ ተፎካካሪ ፓርቲዎችን በማሳተፍ በሃሳብ ክርክር የዘለቀና ድምፅ ለመስጠትም በርካታ ዜጎች የተመዘገቡበት የተሳተፉበት ነበር። በድምጽ አሰጣጡ ወቅት ዜጎች ዝናብ፣ ብርድና ፀሃይ ሳይበግራቸው ከማለዳ እስከ ሌሊት ድምፅ የሰጡበት ታሪካዊ ክስተትም ነበር ። ስለምርጫው አሳታፊነትና ዴሞክራሲያዊነትም እራሳቸው የምርጫው ተወዳዳሪ ተፎካካሪ ፓርቲዎችን ጨምሮ የኢትዮጵያ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት እንዲሁም ሌሎች ታዛቢዎችም ያረጋገጡት ነው።

የብዝሃ ሀሳብ እመርታዎች

በሌላ መልኩ በአንድ ሀገር ውስጥ አካታችና አሳታፊ የፖለቲካ ስርዓት መገንባት የህግ የበላይነትንና የዴሞክራሲ ተቋማትን ለማጠናከር ያለው አስተዋጽኦ ከፍተኛ ነው። ከዚህ አኳያ ባለፉት ዓመታት በኢትዮጵያ ለዲሞክራሲ ተቋማት መጠናከርና ለህግ የበላይነት መከበር በትኩረት መስራት በመቻሉ ውጤቶች ተመዝግበዋል።

ሌላው የአሳታፊ እና አካታች የፖለቲካ ስርዓት መዘርጋት ትሩፋት በሀገሪቱ የፖለቲካ ዋስትና እና መተማመንን መገንባት ነው። በዚህም የፖለቲካ አሳታፊነትን ማጎልበት በመንግስት እና በህዝብ መካከል ያለውን መተማመን በማጎልበት ህዝቡ በመንግስት ፖሊሲዎች ትግበራ ላይ በባለቤትነት ስሜት እንዲሳተፍ ዕድል ይፈጥራል። ለዚህ አብነት ባለፉት ስምንት ዓመታት የተከናወኑ የፕሮጀክት አፈጻጸሞችን መጥቀስ ይቻላል።

ባለፉት ዓመታት የመደመር መንግስት በማቀድ እና የስራ ባህልን በመቀየር በርካታ ስኬቶችን አስመዝግቧል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (/) በቅርቡ በሞጆ የተገነባውን ዘመናዊ የሎጂስቲክስ ማዕከል ማስፋፊያ የመጀመሪያ ምዕራፍ መርቀው ስራ ባስጀመሩበት ወቅት ባስተላለፉት መልዕክትእናልማለን፤ እንተጋለን፤ እንፈጽማለንሲሉ መናገራቸው መንግስት የልማት ፖሊሲዎቹን በውጤታማነት ለመፈጸም ከህዝብ ጋር ምን ያህል ተቀራርቦ እየሰራ መሆኑን የሚያረጋግጥ ነው።

የአንድ ሀገር የኢኮኖሚ እድገት ከሀገሪቱ የፖለቲካ መረጋጋትና አካታችነት ጋር ቀጥተኛ ግንኙነትም አለው። ለዚህ ነውየኢንቨስትመንት ትልቁ ግብዓቱ ሰላም ነውሲሉ የምጣኔ ሀብት ምሁራን የሚገልጹት። ሰላምና ፍትህ በሰፈነበት፣ አካታች የፖለቲካ ስርዓት ባለበት ሀገር ውስጥ ሀገር በቀል እና የውጭ ኢንቨስትመንት ይስፋፋል። ይህም ለስራ እድል ፈጠራ እና ለሀገር ሀብት ማደግ ከፍተኛ አስተዋፅኦ ያበረክታል። ይህን ከግምት በማስገባት ነው መንግስት ባለፉት ዓመታት የፀጥታ ዘርፉን ሪፎርም በማድረግ ለኢንቨስትመንት ዕድገት ምቹ ምህዳር የፈጠረው።

በአንድ ሀገር አካታች እና አሳታፊ የፖለቲካ ስርዓት መትከል ሙስናን ለመከላከል እና የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ለመፍታት የራሱን ሚና ይጫወታል። ባለፉት ዓመታት በተደረጉ ጥረቶች መንግስት ሙስናን ለመከላከል ያለውን ቁርጠኝነት በተግባር በማሳየት በሀገር ሀብት ላይ ምዝበራ በሚፈጽሙ እንዲሁም የመልካም አስተዳደር ችግሮችን በመፍጠር ህዝብ ተገቢውን የመንግስት አገልግሎቶች እንዳያገኝ በሚያደርጉ አካላት ላይ እርምጃ ሲወስድ መቆየቱ ይታወሳል። በዚህም የመንግስት አገልግሎት አሰጣጠን ማዘመን የሚያስችሉ አሰራሮችን በመከተል መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎትን በመዘርጋት ከፍተኛ የተገልጋይ እርካታን በማስገኘት ላይ ይገኛል።

ባለፉት ዓመታት መንግስት አሳታፊ እና አካታች የፖለቲካ ስርዓትን በመተግበር በመንግስት አሰራር እና አገልግሎት አሰጣጥ ላይ ህዝብ የመቆጣጠር ሚናውን እንዲወጣ፣ የሲቪክ ማህበራት ክትትል እንዲያደርጉ በማበረታታት የመልካም አስተዳደር እጦትንና ሙስናን ለመቀነስ በመሰራቱ አመርቂ ውጤቶች ተመዝግበዋል።

እንደ ማጠቃለያ

በአጠቃላይ፣ በኢትዮጵያ የፖለቲካ ስርዓት ውስጥ አሳታፊነትና አካታችነትን ማረጋገጥ አማራጭ ሳይሆን ግዴታ መሆኑን ባለፉት ዓመታት መንግስት በየዘርፎቹ የዜጎች ተሳትፎ እንዲያድግና አካታችነት እንዲረጋገጥ ያከናወናቸው ተግባራት እና የተመዘገቡት ውጤቶች አመላካች ናቸው። የፖለቲካ ምህዳሩን በማስፋት የሁሉም ዜጎች ድምፅ እንዲሰማ ማድረግ የሀገሪቱን ሰላም ዘላቂ፤ ዕድገቷን አሁን ካለበት የፍጥነት ደረጃ የላቀ በማድረግ ወደ ተሻለ የዲሞክራሲ፣ የፍትህ እና የሁለንተናዊ ብልፅግና እና የማንሰራራት ማማ እንድትሸጋገር ያስችላታል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም