ቀጥታ፡

የዘንድሮ ኢሬቻ መስከረም 23 እና 24 ይከበራል

ቢሾፍቱ፤ መስከረም 12/2019 (ኢዜአ)፦ የዘንድሮ ኢሬቻ መስከረም 23 እና 24 ቀን 2019 ዓ.ም እንደሚከበር የኦሮሞ አባገዳዎች ህብረት አስታወቀ።

በዚሁ መሰረት የሆራ ፊንፊኔ ኢሬቻ መስከረም 23 ቀን፣ እንዲሁም የሆራ አርሰዲ ኢሬቻ መስከረም 24 ቀን እንደሚከበር ተገልጿል።

የኢሬቻ በዓል የምስጋና፣ የፍቅር፣ የአንድነት እና የህዝቦች አብሮነት በዓል በመሆኑ፣ ባህሉንና እሴቱን ጠብቆ የሀገርን ገጽታ በሚያጎላ መልኩ መከበር እንዳለበት ተገልጿል።

የ2019 ዓ.ም የኢሬቻ በዓል "ኢሬቻ ለሀገራዊ መግባባት" በሚል መሪ ሐሳብ ይከበራል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም