ቀጥታ፡

የካይሮ እውነተኛ ገጽታ-ከውሃ አባካኝነት እስከ ቀጣናዊ የሰላም ጠንቅ


✍️ግብፅ በዓለም አቀፍ መድረክ የምታቀርበው "የውሃ እጥረት ስጋት አለብኝ" የሚል ተበዳይ አስመስሎ የመቅረብ ትርክት፣ ከጀርባው ያለውን እውነተኛ የስግብግብነትና የቀጣናዊ የበላይነት ፍላጎት ለመሸፈን የተዘጋጀ ጭምብል ነው።

✍️ካይሮ በመቶዎች ለሚቆጠሩ ዓመታት የሚበቃት ግዙፍ የከርሰ ምድር ውሃ እያላትና የዓባይን ውሃ በበረሃ ላይ በማፍሰስ፣ በሌላ በኩል ግን ኢትዮጵያውያን ለዕለት ጉርሳቸውና ለቤታቸው መብራት እንኳ ውሃ እንዳይጠቀሙ፣ የታችኛው የተፋሰስ ሀገራትም በድህነት እንጂ በዕድገት እንዳይገለፁ ትታገላለች።

✍️ግብጽ ለዘመናት የሚበቃ የከርሰ ምድር ውሃ አላት። በኢትዮጵያ ውስጥ ለብዙ ዓመታት ዝናብ ቢቋረጥ እንኳ ግብጽ ለዘመናት የሚበቃት የከርሰ ምድር ውሃ ሀብት ይዛለች።

✍️ግብጽ ውሃ ታባክናለች፤ አጠቃቀሟም እጅግ የከፋ ነው።

✍️ግብፅ ሰፊ ረግረጋማ መሬት ያላት በማስመሰል የሸንኮራ አገዳ እና ሩዝ ታመርታለች። ነገር ግን እሷ የውሃ ማባከኗን ለማስቀጠል ሌሎች ንጹሕ ውሃ እንኳ እንዳይጠጡና የጓሮ ጎመን እንዳያመርቱ መሻቷ ነው።

✍️ግብፅ የዜጎቿን የተደላደለና ቅንጡ ሕይወት ለማስጠበቅ ስትል፣ ኢትዮጵያ ልማቷን ገትታ በድህነት እንድትማቅቅ ትፈልጋለች።

✍️ በበረሃ ውሃ እያፈሰሰች ኢትዮጵያውያን መብራት እንዳያገኙ ትቃወማለች፡ አዳዲስ የቅንጦት ከተሞችን በመገንባት ፤ በሌላ በኩል ግን ኢትዮጵያውያን በቤታቸው መብራትና ማብሰያ ምድጃ እንኳ እንዳይኖራቸው ትሰራለች።

✍️ግብፃውያን የውኃ እጥረት እንዳለባቸው ያስመስላሉ ነገር ግን የዓባይን ውሃ ፍሰት ለመጠበቅ ከ50 ቢሊዮን በላይ ችግኞችን እየተከለች ያለቸውን ኢትዮጵያን ለማመስገን አይፈልጉም። ይልቁንም ግብፅ የኢትዮጵያን ሰላምና አንድነት ለማናጋት ያልፈነቀለችው ድንጋይ የለም።

✍️ግብጽ የሱዳንን ሉዓላዊነትና አንድነት አትሻም። ሱዳንን እንደ ገለልተኛ አገር ሳይሆን እንደ እራሷ ጥገኛ ሀገር አድርጋ ስለምትቆጥራት በውስጥ ጉዳዮቿ እንደፈለገች በመግባት እና ቅጥረኞችን በመጠቀም ሱዳንን ለማፍረስና ኢትዮጵያን የማዳከሚያ መተላለፊያ ለማድረግ እየሰራች ነው።

✍️ግብጽ በቀይ ባሕር ያለ ማንኛውም አገር እንዲበለጽግና እንዲያድግ አትፈልግም። ይህ እጅግ አደገኛ የሆነ የአጥፊነትና የቀጣናው ሰላም ጠንቅ የሆነ የፖለቲካ ሴራ ነው!

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም