ቀጥታ፡

ማንችስተር ዩናይትድ ከፉልሃም ጋር አቻ ተለያየ

አዲስ አበባ፤ መስከረም 10/2019 (ኢዜአ)፦ በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ አምስተኛ ሳምንት ማንችስተር ዩናይትድ እና ፉልሃም ያደረጉት ጨዋታ አንድ አቻ በሆነ ውጤት ተጠናቋል።

ማምሻውን በክራቫን ኮቴጅ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ሊሳንድሮ ማርቲኔዝ በ63ኛው ደቂቃ በራሱ መረብ ላይ ያስቆጠረው ግብ ፉልሃምን መሪ አድርጓል።

ማትያስ ኩንሃ በ89ኛው ደቂቃ ከመረብ ላይ ባሳረፈው ጎል ዩናይትድ አቻ ሆኗል።

ከአምስት የሊጉ ጨዋታዎች አንዱን ብቻ ያሸነፈው ማንችስተር ዩናይትድ በአምስት ነጥብ 12ኛ ደረጃን ይዟል።

ካደረጋቸው አምስት ጨዋታዎች ሁለት ነጥብ ብቻ ያገኘው ፉልሃም በበኩሉ 19ኛ ደረጃን ይዞ ወራጅ ቀጠና ውስጥ ይገኛል።

ዛሬ በተደረጉ ሌሎች መርሐ ግብሮች ማንችስተር ሲቲ ሰንደርላንድን 5 ለ 3 በማሸነፍ የሊጉን መሪነት አጠናክሯል።

ሊቨርፑል ቦርንማውዝን 1 ለ 0 ሲረታ ሊድስ ከክሪስታል ፓላስ ያለ ግብ አቻ ተለያይተዋል።

ጨዋታዎቹን ተከትሎ አምስተኛ ሳምንት ተጠናቋል።

የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ በብሔራዊ ቡድኖች ጨዋታ ምክንያት የሚቋረጥ ሲሆን መስከረም 30 ቀን 2019 ዓ.ም በስድስተኛ ሳምንት መርሐ ግብር ይመለሳል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም