ቀጥታ፡

የ"ጊፋታ" በዓል በወላይታ ሶዶ ከተማ በድምቀት እየተከበረ ነው

ወላይታ ሶዶ ፤ መስከረም 10/2019 (ኢዜአ)፦ የ2019 ዓ.ም የወላይታ ዘመን መለወጫ "ጊፋታ" በዓል በወላይታ ሶዶ ሁለገብ ስቴዲየም በተለያዩ ዝግጅቶች እየተከበረ ይገኛል።

የዘንድሮ "ጊፋታ" በዓል በወላይታ ሶዶ ከተማ "የትውልድ ቅርስን እንጠብቅ፣ የጊፋታን ውርስ እናስቀጥል" በሚል መሪ ቃል ነው እየተከበረ የሚገኘው፡፡


 

"ጊፋታ" ኢትዮጵያዊ አንድነትና ህብረት የሚንጸባረቅበት ተራርቀው የቆዩ ዘመድ ወዳጆች የሚቀራረቡበት ፣የተነፋፈቁ የሚገናኙበት፣ የተጣሉ የሚታረቁበት የዕርቅ፣ የፍቅር፣ የአንድነትና የደስታ በዓል ነው።

በ2018 ዓ.ም ታህሳስ ወር ላይ በዩኔስኮ የሰው ልጅ ወካይ ቅርስ ሆኖ ተመዘገበው "ጊፋታ" ከተመዘገበ በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ዛሬ በደማቁ እየተከበረ ነው።


 

በበዓሉ ላይ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርእሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደን ጨምሮ የፌደራል፣ የክልል፣ የዞን፣ የከተማ አስተዳደርና የወረዳ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ የኃይማኖት አባቶች፣ ከሁሉም ኢትዮጵያ ክልሎች የተጋበዙ ተወካዮችና የአካባቢው ነዋሪዎች እየተሳተፉበት ይገኛሉ።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም