ቀጥታ፡

የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የዕለቱ ተጠባቂ መርሐ ግብሮች

አዲስ አበባ፤ መስከረም 10/2019 (ኢዜአ):- የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ አምስተኛ ሳምንት መርሐ ግብር ዛሬ ይጠናቀቃል።

በዕለቱ አራት ጨዋታዎች ይደረጋሉ።

ማንችስተር ሲቲ ከቀኑ 11 ሰዓት ላይ በኢትሃድ ስታዲየም ሰንደርላንድን ያስተናግዳል።

ባለሜዳው ሲቲ በሊጉ ያደረጋቸውን አራት ጨዋታዎች በማሸነፍ በ12 ነጥብ አንደኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።

ሰንደርላንድ በአራት ነጥብ 14ኛ ደረጃን ይዟል።  ቡድኑ ባለፉት ሁለት ጨዋታዎች አላሸነፈም።

ማንችስተር ሲቲ ካሸነፈ  ከአርሰናል ጋር ያለውን የነጥብ ልዩነት ወደ ሶስት ከፍ ያደርጋል።

አርሰናል ትናንት በብራይተን የ3 ለ 0 ሸንፈት አስተናግዷል።

ሰንደርላንድ ወደ አሸናፊነት ለመመለስ በሚያደርገው ጨዋታ ባለሜዳውን ክለብ ይፈትነዋል ተብሎ ይጠበቃል።

በክራቨን ኮቴጅ ስታዲየም ፉልሃም ከማንችስተር ዩናይትድ ከምሽቱ 12 ሰዓት ከ30 ላይ ይጫወታሉ።

ባለሜዳው ፉልሃም በአንድ ነጥብ የመጨረሻውን 20ኛ ደረጃን ይዟል።

ማንችስተር ዩናይትድ በበኩሉ በአራት ነጥብ 13ኛ ደረጃን ይዟል። ቡድኑ ባለፉት ሁለት ጨዋታዎች ድል አልቀናውም።

ፉልሃም በሊጉ የመጀመሪያ ድሉን ለማስመዝገብ ዩናይትድ ወደ አሸናፊነት መንገድ ለመመለስ የሚያደርጉት ጨዋታ ትኩረትን ስቧል።

በሌላኛው መርሐ ግብር ቦርንማውዝ ከሊቨርፑል ከቀኑ 10 ሰዓት ላይ በቫይታሊቲ ስታዲየም ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።

ቦርንማውዝ በሶስት ነጥብ 16ኛ ደረጃን ይዟል። ሊቨርፑል በስድስት ነጥብ 10ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።

ባለሜዳው ቦርንማውዝ በሊጉ የመጀመሪያ ድሉን ለማስመዝገብ ይጫወታል። 

በሊጉ በአንድ ጨዋታ ብቻ ያሸነፈው ሊቨርፑል ወደ አሸናፊነት መንገድ ለመመለስ ወሳኝ ፍልሚያ ያደርጋል።

የ44 ዓመቱ የሊቨርፑል አሰልጣኝ አንዶኒ ኢራኦላ የቀድሞ ክለባቸውን ይገጥማሉ።

ሊድስ ዩናይትድ ከክሪስታል ፓላስ ከቀኑ 10 ሰዓት በኢላንድ ሮድ ስታዲየም ይጫወታሉ።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም