ቀጥታ፡

በዓለም የጎዳና ላይ ሩጫ ሻምፒዮና ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ለሜዳሊያ የሚጠበቁባቸው የፍጻሜ ውድድሮች ይካሄዳሉ

አዲስ አበባ፤ መስከረም 10/2019 (ኢዜአ):-  ሁለተኛው የዓለም አትሌቲክስ የጎዳና ላይ ሩጫ ሻምፒዮና ዛሬ ፍጻሜውን ያገኛል።

በሻምፒዮናው ማብቂያ ቀን ሁለት የፍጻሜ ውድድሮች ይካሄዳሉ። 

ከረፋዱ 4 ሰዓት ከ10 ላይ የሴቶች ግማሽ ማራቶን ፍጻሜ ይደረጋል።

መሰለች አለማየሁ፣ ፅጌ ገብረሰላማ፣ ዝማም ባራኪና ፍታው ዘራይ ኢትዮጵያን ወክለው የሚሳተፉ አትሌቶች ናቸው።

የወንዶች የግማሽ ማራቶን ፍጻሜ ውድድር ከረፋዱ 4 ሰዓት ከ45 ላይ ይከናወናል።

በላይ ጥላሁን፣ በረከት ነጋ፣ ባየልኝ ተሻገር እና ታደሰ ወርቁ በውድድሩ ላይ ይሳተፋሉ።

በሁለቱም ውድድሮች ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ለሜዳልያ ይጠበቃሉ።

ኢትዮጵያ ትናንት በሻምፒዮናው መክፈቻ ቀን አንድ የወርቅ እና አንድ የብር ሜዳሊያ አግኝታለች።

ሁለተኛው የዓለም አትሌቲክስ የጎዳና ላይ ሩጫ ሻምፒዮና ዛሬ ፍጻሜውን ያገኛል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም