ቀጥታ፡

አርሰናል በሊጉ የመጀመሪያ ሽንፈቱን አስተናገደ

አዲስ አበባ፤ መስከረም 9/2019 (ኢዜአ):- በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የአምስተኛ ሳምንት መርሐ ግብር ብራይተን አርሰናልን 3 ለ 0 አሸንፏል።

በአሜክስ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ፓስካል ግሮስ፣ ቻራላምፖስ ኮስቱላስ እና ቼማ አንድሬስ ግቦቹን አስቆጥረዋል።

ባለሜዳው ብራይተን በተጋጣሚው ላይ ብልጫ ወስዶ ተጫውቷል።

የወቅቱ የሊጉ ሻምፒዮን አርሰናል የጨዋታ እንቅስቃሴ ጥሩ የሚባል አልነበረም።


 

ጨዋታውን ተከትሎ አርሰናል በሊጉ የመጀመሪያ ሽንፈቱን ያስተናገደ ሲሆን የሊጉን መሪነትም ለማንችስተር ሲቲ አስረክቧል።

መድፈኞቹ በ12 ነጥብ ሁለተኛ ደረጃ ላይ ይገኛሉ።

በውድድር ዓመቱ ሶስተኛ ድሉን ያስመዘገበው ብራይተን በበኩሉ በ10 ነጥብ ደረጃውን ከ6ኛ ወደ 3ኛ ከፍ አድርጓል።

በሌሎች መርሐ ግብሮች ኒውካስትል ዩናይትድ ሁል ሲቲን 2 ለ 1 ፣ ኤቨርተን ኤፕስዊች ታውንን 1 ለ 0 አሸንፈዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም