አስቶንቪላ ቶተንሃምን በመርታት የመጀመሪያ የሊግ ድሉን አስመዘገበ - ኢዜአ አማርኛ
አስቶንቪላ ቶተንሃምን በመርታት የመጀመሪያ የሊግ ድሉን አስመዘገበ
አዲስ አበባ፤ መስከረም 9/2019 (ኢዜአ):-በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የአምስተኛ ሳምንት መርሐ ግብር አስቶንቪላ ቶተንሃም ሆትስፐርስን 3 ለ 2 አሸንፏል።
በቶተንሃም ሆትስፐርስ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ጆሃን ማንዛምቢ፣ ኒኮላስ ጃክሰን እና ኤሚሊያኖ ቡንዲያ ግቦቹን ከመረብ ላይ አሳርፈዋል።
ኮኖር ጋላገር እና ጃን ፓውል ቫን ሄከ ለቶተንሃም ግቦቹን አስቆጥረዋል። ይህን ቡድኑ በውድድር ዓመቱ ያስቆጠራቸው የመጀመሪያ ግቦች ሆነዋል።
ባለሜዳው ቶተንሃም በመጀመሪያው አጋማሽ ያገኛቸውን የግብ እድሎች አለመጠቀሙ ዋጋ አስከፍሎታል።
አስቶንቪላ ከእረፍት መልስ የተሻለ እንቅስቃሴ በማድረግ ግቦቹን አስቆጥሯል።
በሊጉ የመጀመሪያ ድሉን ያስመዘገበው አስቶንቪላ በአራት ነጥብ ከ19ኛ ወደ 14ኛ ከፍ ብሏል።
በውድድር ዓመቱ ሶስተኛ ሽንፈቱን ያስተናገደው ቶተንሃም ሆትስፐርስ በሁለት ነጥብ ከነበረበት 17ኛ ደረጃ ወደ 18ኛ ዝቅ በማለት ወራጅ ቀጠና ውስጥ ገብተዋል።
በክረምቱ የተጫዋቾች የዝውውር መስኮት 334 ሚሊዮን ፓውንድ ያወጣው ቶተንሃም በውጤት ማጣት ጉዞው ቀጥሏል።