አትሌት ልቅና አምባው በዓለም የጎዳና ላይ ሩጫ ሻምፒዮና የመጀመሪያውን የወርቅ ሜዳሊያ ለኢትዮጵያ አስገኘች - ኢዜአ አማርኛ
አትሌት ልቅና አምባው በዓለም የጎዳና ላይ ሩጫ ሻምፒዮና የመጀመሪያውን የወርቅ ሜዳሊያ ለኢትዮጵያ አስገኘች
አዲስ አበባ፤ መስከረም 9/2019 (ኢዜአ):- በሁለተኛው የዓለም አትሌቲክስ የጎዳና ላይ ሩጫ ሻምፒዮና የአምስት ኪሎ ሜትር ሴቶች የፍጻሜ ውድድር አትሌት ልቅና አምባው አሸናፊ ሆናለች።
ልቅና 14 ደቂቃ ከ41 ሴኮንድ የገባችበት ሰዓት ነው።
አለሽኝ ባወቀ አምስተኛ ደረጃን ይዛ አጠናቃለች።
በወንዶች አምስት ኪሎ ሜትር ውድድር አዲሱ ይሁኔ ስድስተኛና መዝገቡ ስሜ ሰባተኛ ደረጃን ይዘው አጠናቀዋል።
ዛሬ በሴቶች በተካሄደው የአንድ ማይል የፍጻሜ ውድድር አትሌት ፍሬወይኒ ኃይሉ 4 ደቂቃ ከ24 ሴኮንድ ከ35 ማይክሮ ሴኮንድ ሁለተኛ በመውጣት የብር ሜዳሊያ ለኢትዮጵያ ማስገኘቷ የሚታወስ ነው።