ኢትዮጵያ በዓለም የጎዳና ላይ ሩጫ ሻምፒዮና የመጀመሪያውን ሜዳሊያ አገኘች - ኢዜአ አማርኛ
ኢትዮጵያ በዓለም የጎዳና ላይ ሩጫ ሻምፒዮና የመጀመሪያውን ሜዳሊያ አገኘች
አዲስ አበባ፤ መስከረም 9/2019 (ኢዜአ):- ሁለተኛው የዓለም አትሌቲክስ የጎዳና ላይ ሩጫ ሻምፒዮና ዛሬ በዴንማርክ ኮፐንሃገን ተጀምሯል።
በሴቶች በተካሄደው የአንድ ማይል የፍጻሜ ውድድር አትሌት ፍሬወይኒ ኃይሉ 4 ደቂቃ ከ24 ሴኮንድ ከ35 ሴኮንድ ሁለተኛ በመውጣት የብር ሜዳሊያ ለኢትዮጵያ አስገኝታለች።
ይህም ኢትዮጵያ በሻምፖዮናው ያገኘቸው የመጀመሪያ ሜዳሊያ ሆኖ ተመዝግቧል።
አትሌት ፍሬወይኒ በርቀቱ የዓመቱን ፈጣን ሰዓቷን አስመዝግባለች።
ሌላኛዋ ኢትዮጵያዊ አትሌት ብርቄ ኃየሎም 29ኛ ደረጃን ይዛ አጠናቃለች።
ፈረንሳዊቷ አጋቴ ጊልሞት 4 ደቂቃ ከ22 ሴኮንድ ከ74 ማይክሮ ሴኮንድ በርቀቱ የዓመቱን የዓለም ፈጣን ሰዓት በማስመዝገብ አሸናፊ ሆናለች።
ኬንያዊቷ አትሌት ሚሪየም ቼሮፕ ሶስተኛ ወጥታለች።