ለሴቶች ኦሊምፒክ ማጣሪያ ለ34 ተጫዋቾች ጥሪ ቀረበ - ኢዜአ አማርኛ
ለሴቶች ኦሊምፒክ ማጣሪያ ለ34 ተጫዋቾች ጥሪ ቀረበ
አዲስ አበባ፤ መስከረም 9/2019 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን ዋና አሰልጣኝ ቻለው ለሜቻ በሎስ አንጀለስ የ2028 ኦሊምፒክ ማጣርያ ከሩዋንዳ ጋር ለሚያደርገው ጨዋታ ዝግጅት ለ34 ተጫዋቾች ጥሪ አድርገዋል።
ጥሪ የተደረገላቸው ተጫዋቾች ከነገ ጀምሮ በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፅሕፈት ሪፖርት እንዲያደርጉ ጥሪ ቀርቧል።
የማጣሪያ ጨዋታዎቹ መስከረም 25 እና ጥቅምት 3 ቀን 2019 ዓ.ም ይካሄዳሉ።
ቻለው ለሜቻ በሁለት ዓመት ውል ትናንት የብሔራዊ ቡድኑ አሰልጣኝ ሆነው መሾማቸው የሚታወስ ነው።