ቻለው ለሜቻ የኢትዮጵያ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን ዋና አሰልጣኝ ሆነው ተሾሙ - ኢዜአ አማርኛ
ቻለው ለሜቻ የኢትዮጵያ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን ዋና አሰልጣኝ ሆነው ተሾሙ
አዲስ አበባ ፤ መስከረም 8/2019 (ኢዜአ) ፡- አሰልጣኝ ቻለው ለሜቻ የኢትዮጵያ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን ዋና አሰልጣኝ ሆነው ተሹመዋል።
አሰልጣኙ ለሁለት ዓመት የሚያቆይ ውል መፈራረማቸውን የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አስታውቋል።
ቻለው ለሜቻ ከዚህ ቀደም የኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች ሴቶች ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ በመሆን ሰርተዋል።
በተጨማሪም በኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ የሚወዳደረው የቦሌ ክፍለ ከተማ አሰልጣኝ የነበሩ ሲሆን በኢትዮጵያ ስፖርት አካዳሚም በስፖርት ሳይንስ ባለሙያነት አገልግለዋል።