ቀጥታ፡

ብሬንትፎርድ ከቼልሲ፤የሊጉ የአምስተኛ ሳምንት የመጀመሪያ ጨዋታ

አዲስ አበባ፤ መስከረም 8/2019 (ኢዜአ):- የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ አምስተኛ ሳምንት መርሐ ግብር ዛሬ ይጀመራል።

ምሽት አራት ሰዓት ላይ ብሬንትፎርድ ከቼልሲ በጂቴክ ኮሙኒቲ ስታዲየም ይጫወታሉ።

ባለሜዳው ብሬንትፎርድ በስድስት ነጥብ ሰባተኛ ደረጃን ይዟል።

ተጋጣሚው ቼልሲ በሰባት ነጥብ ስድስተኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።

ሁለቱ የለንደን ክለቦች በፕሪሚየር ሊጉ ሲገናኙ የአሁኑ ለ11ኛ ጊዜ ነው።

ከዚህ ቀደም ባደረጓቸው 10 ጨዋታዎች ቼልሲ በአራቱ ድል ሲቀናው ብሬንትፎርድ ሶስት ጊዜ አሸንፏል። በቀሪ ሶስት ጨዋታዎች አቻ ተለያይተዋል።

ቼልሲ በ10ሩ ጨዋታዎች ላይ 15 ግቦችን ከመረብ ላይ ሲያሳርፍ ብሬንትፎርድ 12 ጎሎችን አስቆጥሯል።

ቡድኖቹ ለመጨረሻ ጊዜ በሊጉ የተገናኙት እ.አ.አ ጃንዋሪ 2026 ሲሆን በወቅቱ ቼልሲ በኮል ፓልመር እና ጆአኦ ፔድሮ ግቦች 2 ለ 0 አሸንፏል።

ብሬንትፎርድ ባለፉት ሶስት ጨዋታዎች፣ ቼልሲ ደግሞ ባለፉት ሁለት የሊግ መርሐ ግብሮች ማሸነፍ አልቻሉም።

የለንደኖቹ ክለቦች ወደ አሸናፊነት ለመመለስ የሚያደርጉት ጨዋታ ተመጣጣኝ ፉክክር ይታይበታል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ አምስተኛ ሳምንት መርሐ ግብር እስከ መስከረም 10 ቀን 2019 ዓ.ም ይቆያል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም