ቀጥታ፡

የወቅቱ ሻምፒዮን ማንችስተር ሲቲ በካራባኦ ካፕ ወደ ቀጣዩ ዙር አለፈ

አዲስ አበባ፤ መስከረም 7/2019 (ኢዜአ)፦ በካራባኦ ካፕ የሶስተኛ ሳምንት መጨረሻ መርሐ ግብር ማንችስተር ሲቲን ኖርዊች ሲቲን 5 ለ 0 በሆነ ሰፊ የግብ ልዩነት አሸንፏል።

ማምሻውን በኢትሃድ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ፍሎይድ ሳምባ ሁለት ግቦቹን ሲያስቆጥር ራያን ቸርኪ፣ አለን እና ራያን ማኪዱ ቀሪዎቹን ጎሎች ከመረብ ላይ አሳርፈዋል።

የ17 ዓመቱ ፍሎይድ ሳምባ የቀድሞው የአስቶንቪላ እና ብላክበርን ሮቨርስ ተጫዋች ክርስቶፈር ሳምባ ልጅ ነው።

በጨዋታው ማንችስተር ሲቲ ከፍተኛ የጨዋታ ብልጫ ወስዷል።

የወቅቱ የውድድሩ አሸናፊ ማንችስተር ሲቲ ወደ አራተኛ ዙር አልፏል።

በእንግሊዝ ሻምፒዮንሺፕ የሚገኘው ኖርዊች ሲቲ ጉዞው ሶስተኛ ዙር ላይ ተገቷል።

የአራተኛ ዙር ድልድል ትናንት ማምሻውን የወጣ ሲሆን ማንችስተር ሲቲ ከብራይተን ጋር ይጫወታል።

ሊቨርፑል ከቼልሲ፣ ፍሊትውድ ከአርሰናል፣ ፉልሃም ከክሪስታል ፓላስ፣ ቦርንማውዝ ከአስቶንቪላ፣ ሰንደርላንድ ከብሬንትፎርድ፣ ኤቨርተን ከኒውካስትል ዩናይትድ እና ብራድፎርድ ሲቲ ከፒተርቦሮው ዩናይትድ ሌሎች የሚደረጉ የአራተኛ ዙር ጨዋታዎች ናቸው።

የአራተኛ ዙር መርሐ ግብር ከጥቅምት 16 እስከ 22 ቀን 2019 ዓ.ም ይካሄዳል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም