የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ ግብር ይፋ ሆነ - ኢዜአ አማርኛ
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ ግብር ይፋ ሆነ
አዲስ አበባ፤ መስከረም 7/2019 (ኢዜአ)፦ የ2019 ዓ.ም የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ ግብር የእጣ ማውጣት ስነ ስርዓት ዛሬ ተካሄዷል።
በፕሪሚየር ሊጉ የሚሳተፉ 18 ክለቦች በስድስት ቋቶች ተከፍለው የእጣ የማውጣት ሂደቱ ተከናውኗል።
በዚሁ መሰረት የወቅቱ የሊጉ አሸናፊ ሲዳማ ቡና በመጀመሪያ ሳምንት ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጋር ይጫወታል።
ቅዱስ ጊዮርጊስ ከነገሌ አርሲ፣ ኢትዮጵያ ቡና ከሸገር ከተማ፣ ሀዋሳ ከተማ ከመቻል፣ ወላይታ ድቻ ከፋሲል ከነማ፣ጋሞ ጨንቻ ከኢትዮጵያ መድን፣ ሀላባ ከተማ ከወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ፣ ኢትዮ ኤሌክትሪክ ከአዳማ ከተማ እና ሀዲያ ሆሳዕና ከባህር ዳር ከተማ ሌሎች በመጀመሪያ ሳምንት የሚደረጉ ጨዋታዎች ናቸው።
በሁለተኛ ሳምንት ቅዱስ ጊዮርጊስ ከኢትዮጵያ ቡና የሚያደርጉት የደርቢ ጨዋታ ተጠባቂ ነው።
የፕሪሚየር ሊጉ ጨዋታዎች በሰባት የተመረጡ ስታዲየሞች ይደረጋሉ።
አዲስ አበባ ስታዲየም፣ አዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርስቲ ስታዲየም፣ ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም፤ ባህርዳር አለም አቀፍ ስታዲየም፣ሀላባ ስታዲየም፣ ሆሳዕና አብዩ ኤርሳሞ ስታዲየም እና አርባምንጭ ዩንቨርሲቲ አባያ ካምፓስ ስታዲየም ውድድሩ የሚካሄድባቸው ሜዳዎች ናቸው።
ፕሪሚየር ሊጉ መስከረም 29 ቀን 2019 ዓ.ም ይጀመራል።