የኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን አቻ ተለያየ - ኢዜአ አማርኛ
የኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን አቻ ተለያየ
አዲስ አበባ፤ መስከረም 7/2019 (ኢዜአ)፦ ከ20 ዓመት በታች የአፍሪካ ዋንጫ የሴካፋ ዞን ማጣሪያ ኢትዮጵያ ከሩዋንዳ ጋር ያለ ግብ አቻ ተለያይታለች።
ጨዋታው በታንዛንያ በሚገኘው አሁሩ ስታዲየም ተካሄዷል።
ውጤቱን ተከትሎ ኢትዮጵያ የመጀመሪያ ነጥቧን አግኝታለች።
ብሔራዊ ቡድኑ ሁለተኛ ጨዋታውን መስከረም 9 ቀን 2019 ዓ.ም ከአዘጋጇ ታንዛንያ ጋር ያደርጋል።
በዚሁ ምድብ ከትናንት በስቲያ በተካሄደው ጨዋታ ታንዛንያ ሩዋንዳን 3 ለ 0 አሸንፋለች።
ኢትዮጵያ ወደ ግማሽ ፍጻሜው ለማለፍ ታንዛንያን ማሸነፍ ይጠበቅበታል።
ከ20 ዓመት የአፍሪካ ዋንጫ የሴካፋ ዞን ማጣሪያ ከመስከረም 5 ቀን 2019 ዓ.ም አንስቶ እየተካሄደ ይገኛል።
በውድድሩ ዘጠኝ ሀገራት በሶስት ምድብ ተከፍለው ጨዋታቸውን በማድረግ ላይ ናቸው።
በማጣሪያው ለፍጻሜ የሚደርሱት ሁለት ሀገራት እ.አ.አ በ2027 በጋና ለሚካሄደው ከ20 ዓመት በታች የአፍሪካ ዋንጫ ቀጣናውን ወክለው ይሳተፋሉ።
የሴካፋ ዞን ማጣሪያ እስከ መስከረም 15 ቀን 2019 ዓ.ም ይቆያል።