ቀጥታ፡

የኢትዮጵያ ወጣቶች በሩሲያ የዓለም ወጣቶች ፌስቲቫል ላይ የኢትዮጵያን ውብ ባህል አስተዋወቁ

አዲስ አበባ ፤መስከረም 6/2019(ኢዜአ)፦የኢትዮጵያ ወጣት ልዑካን በሩሲያ እየተካሄደ ባለው የዓለም ወጣቶች ፌስቲቫል ላይ የሀገራቸውን ውብ የባህል ሀብት፣ ታሪካዊ ቅርሶች፣ የቱሪዝም መስህቦች እና ልዩ ሀገራዊ መታወቂያዎችን ለዓለም አቀፉ ማሕበረሰብ አስተዋውቀዋል።


 

ወጣቶቹ በዚህ ታላቅ ዓለም አቀፍ መድረክ ከተለያዩ የዓለም ክፍሎች ከተወጣጡ ወጣቶች ጋር በነበራቸው የጠበቀ ግንኙነት የኢትዮጵያን ጥንታዊ ታሪክ፣ የእንግዳ ተቀባይነት ባህል እና የመስህብ ስፍራዎችን በሚገባ ማስገንዘባቸውን የቱሪዝም ሚኒስቴር መረጃ አመላክቷል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም