ቀጥታ፡

አርሰናል እና ሊቨርፑል በካራባኦ ካፕ ወደ ቀጣዩ ዙር አለፉ

አዲስ አበባ፤ መስከረም 5/2019 (ኢዜአ)፦ በእንግሊዝ ካራባኦ ካፕ የሶስተኛ ዙር ጨዋታዎች ማምሻውን ተካሄደዋል።

በፖርትማን ሮድ በተደረገው ጨዋታ አርሰናል ኤፕስዊች ታውንን 4 ለ 2 ረትቷል።

የ16 ዓመቱ ታዳጊ ማክስ ዶውማን ሁለት ግቦችን ሲያስቆጥር ኖኒ ማዱዌኬ እና ሚኬል ሜሪኖ ቀሪዎቹን ጎሎች ከመረብ ላይ አሳርፈዋል።

አኒስ ሜህመቲ እና ቹባ አክፖም የኤፕስዊችን ግቦች አስቆጥረዋል።

በሌላኛው መርሐ ግብር ሊቨርፑል ቶተንሃም ሆትስፐርስን 3 ለ 1 አሸንፏል።

በአንፊልድ ሮድ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ አሌክሲስ ማካሊስተር፣ ኮዲ ጋፕኮ እና ዶምኒክ ስቦዝላይ የማሸነፊያ ግቦቹን አስቆጥረዋል።

ኮኖር ጋላገር የቶተንሃምን ጎል ከመረብ ላይ አሳርፏል።

ብሬንትፎርድ ሬዲንግን 2 ለ 1፤ ፉልሃም ዌስትሃም ዩናይትድን 3 ለ 2 አሸንፈዋል።

ፒተርቦሮው ባርንስሌይን በመለያ ምት ረትቷል።

ውጤቱን ተከትሎ አርሰናል፣ ሊቨርፑል፣ ብሬንትፎርድ፣ ፉልሃም እና ፒተርቦሮው ወደ አራተኛ ዙር አልፈዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም