ቀጥታ፡

አቶ ኢሳያስ ጅራ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት በመሆን ለሶስተኛ ጊዜ ተመረጡ

አዲስ አበባ፤መስከረም 5/2019 (ኢዜአ):- አቶ ኢሳያስ ጅራ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት በመሆን ለሶስተኛ ጊዜ ተመርጠዋል።

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን 18ኛ መደበኛ እና የምርጫ ጠቅላላ ጉባዔ በአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን /ECA/ እየተካሄደ ይገኛል።

ጠቅላላ ጉባኤው ብቻቸውን በእጩነት የቀረቡትን አቶ ኢሳያስ ጅራን ለቀጣይ አራት ዓመታት ፌዴሬሽኑን በፕሬዝዳንትነት እንዲመሩ መርጧል።

አቶ ኢሳይያስ ጅራ ከተሰጡ 88 ድምፆች መካከል 81ዱን ማግኘታቸውን ፌዴሬሽኑ አስታውቋል።

የካፍ የሥራ አስፈጻሚ እና የፊፋ ቋሚ ኮሚቴ አባል የሆኑት አቶ ኢሳያስ ጅራ ከግንቦት 2010 ዓ.ም አንስቶ ፌዴሬሽኑን በፕሬዝዳንትነት እየመሩ ይገኛል።

በተያያዘም አቶ አለሙ መግራ የፌዴሬሽኑ ምክትል ፕሬዝዳንት ሆነው ተመርጠዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም