ሊድስ ዩናይትድ ደረጃውን ወደ ሶስተኛ ከፍ ያደረገበትን ድል አስመዘገበ - ኢዜአ አማርኛ
ሊድስ ዩናይትድ ደረጃውን ወደ ሶስተኛ ከፍ ያደረገበትን ድል አስመዘገበ
አዲስ አበባ ፤ መስከረም 5/2019 (ኢዜአ)፦ በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ አራተኛ ሳምንት መርሐ ግብር ሊድስ ዩናይትድ ኒውካስትል ዩናይትድን 4 ለ 1 በሆነ ሰፊ የግብ ልዩነት አሸንፏል።
ማምሻውን በኢላንድ ሮድ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ጄይደን ቦግል፣ ዶምኒክ ካልቨርት-ልዊን፣ ኖህ ኦካፎር እና የኒውካስትሉ ሉዊስ ማይሊ በራሱ ላይ ግቦቹን አስቆጥረዋል።
ባዙማና ቱሬ ለኒውካስትል የማስተዛዘኛውን ጎል ከመረብ ላይ አሳርፏል።
ባለሜዳው ሊድስ በመጀመሪያው አጋማሽ የወሰደውን ከፍተኛ ብልጫ በሚገባ በመጠቀም ሶሰት ግቦችን ሲያስቆጥር ከእረፍት መልስ አንድ ጎል ከመረብ ላይ አሳርፏል።
ኒውካስትል ዩናይትድ ደካማ የጨዋታ እንቅስቃሴ አድርጓል።
በሊጉ ሁለተኛ ድሉን ያስመዘገበው ሊድስ ዩናይትድ በስምንት ነጥብ ከ11ኛ ደረጃ ወደ 3ኛ ከፍ ብሏል። ቡድኑ በሊጉ እስከ አሁን ሽንፈት አላስተናገደም።
በውድድር ዓመቱ የመጀመሪያ ሽንፈቱን ያስተናገደው ኒውካስትል በአምስት ነጥብ 12ኛ ደረጃን ይዟል።
ጨዋታውን ተከትሎ አራተኛ ሳምንት ተጠናቋል።
የአምስተኛ ሳምንት መርሐ ግብር ከመስከረም 8 ቀን 2019 ዓ.ም አንስቶ ይካሄዳል።