በሳምንቱ መጨረሻ በተደረጉ ዓለም አቀፍ የአትሌቲክስ ውድድሮች ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ድል ቀንቷቸዋል - ኢዜአ አማርኛ
በሳምንቱ መጨረሻ በተደረጉ ዓለም አቀፍ የአትሌቲክስ ውድድሮች ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ድል ቀንቷቸዋል
አዲስ አበባ፤ መስከረም 4/2019 (ኢዜአ)፦በሳምንቱ መጨረሻ ቀናት በተከናወኑ የጎዳና ላይ ውድድሮች ኢትዮጵያውያን አትሌቶች አሸንፈዋል።
በታይላንድ በተካሄደው የባንግሳኤን 10 ኪሜ ውድድር በወንዶች አትሌት ሰውመሆን አንተነህ 28:28 በሆነ ጊዜ አሸናፊ ሲሆን፣ አትሌት ገላና ተሾመ 28:40 በማስመዝገብ ሁለተኛ ወጥቷል።
አትሌት ጫለቺሳ ገለታ ደግሞ 29:31 በማስመዝገብ ስድስተኛ ደረጃን ይዟል።
በሴቶች ውድድር አትሌት ውብርስት አስቻለ 32:14 በሆነ ጊዜ ሁለተኛ ስትሆን፣አትሌት ቢቂሌ አመሱ 32:31 በማስመዝገብ ሦስተኛ ወጥታለች።
አትሌት በቀሽ ኦላኒ 33:14 አራተኛ፣ አትሌት ዱሌ ምትኩ 33:53 ሰባተኛ እና አትሌት ስለእናት ቢተው 33:56 ስምንተኛ ደረጃን ይዘዋል።
በቻይና ሃርቢን ማራቶን በወንዶች አትሌት ያሚ ዳዲ 2:12:41 በሆነ ጊዜ የወንዶችን ውድድር ሲያሸንፍ፣ በሴቶች አትሌት ቡርቱካን ይፍሩ 2:30:19 በሆነ ጊዜ አንደኛ ወጥታለች።
አትሌት ገብሬላ ዮሐንስ 2:30:26 ሁለተኛ፣አትሌት ንፁህ ነገሰ 2:34:01 ሦስተኛ ደረጃን ይዘዋል።
በጀርመን ሙንስተር ማራቶን አትሌት አገሬ በላቸው 2:28:43 በሆነ ጊዜ የሴቶችን ውድድርን አሸንፋለች
አትሌት አዛለች ማረሻ ደግሞ 2:31:09 በማስመዝገብ ሦስተኛ ወጥታለች።
በስሪላንካ ኮሎምቦ ማራቶን አትሌት አይናለም ካሳሁን 2:54:09 በሆነ ጊዜ የሴቶችን ውድድር አሸንፋለች።
አትሌት ጌጤ ጉታ 2:54:48 ሁለተኛ፣አትሌት ገንዘብ ሹሚ 2:55:20 ሦስተኛ በመሆን የኢትዮጵያን የበላይነት አረጋግጠዋል።
በወንዶች አትሌት ነጋሲ ቱጂ ኮርሜ 2:21:50 በሆነ ጊዜ ሦስተኛ ደረጃን ይዞ ጨርሷል።
በእንግሊዝ ግሬት ኖርዝ ግማሽ ማራቶን አትሌት መልክናት ውዱ 1:09:37 በሆነ ጊዜ ሦስተኛ ደረጃን ይዛ ጨርሳለች።
በፖርቹጋል የፖርቶ ግማሽ ማራቶን አትሌት ሕይወት መሐሪ 1:12:07 በሆነ ጊዜ ሦስተኛ ስትወጣ፣ በወንዶች አትሌት ንጉስ መኮንን 1:03:52 በማስመዝገብ አምስተኛ ደረጃን ይዟል።
በታይላንድ ክራቢ ግማሽ ማራቶን ደግሞ አትሌት ፀጋይ ኪሮስ 1:08:58 በሆነ ጊዜ ሁለተኛ፣አትሌት ገመቹ ዲዳ 1:09:15 ሦስተኛ ደረጃን ይዘዋል።
በሴቶች አትሌት ማርታ ብርሃን 1:23:01 በማስመዝገብ ሦስተኛ ወጥታለች።
በስሎቫኪያ በተካሄደው የብሩዝ የምሽት 10 ኪሜ ውድድር አትሌት መልኬነህ አዜዜ 27:40 በሆነ ጊዜ የውድድሩ አሸናፊ ሲሆን፣አትሌት ሽመልስ ንጉሴ 27:50 በማስመዝገብ ሁለተኛ ደረጃን ይዟል።