በዞኑ በምርት ዘመኑ 28 ሚሊዮን ኩንታል ምርት ለመሰብሰብ የሚያስችሉ ተግባራት እየተካሄዱ ነው - ኢዜአ አማርኛ
በዞኑ በምርት ዘመኑ 28 ሚሊዮን ኩንታል ምርት ለመሰብሰብ የሚያስችሉ ተግባራት እየተካሄዱ ነው
ባህር ዳር፤ መስከረም 4/2019 (ኢዜአ)፦ በደቡብ ጎንደር ዞን በመኸር ወቅት ከለማው 641 ሺህ ሄክታር መሬት ላይ ከ28 ሚሊዮን ኩንታል በላይ ምርት ለመሰብሰብ የሚያስችል የተባይ አሰሳና የአረም መከላከል ስራ እየተከናወነ ይገኛል።
የዞኑ ግብርና መምሪያ ኃላፊ አቶ የሺጥላ ፈቃዴ እንደገለጹት፤ በዞኑ በኩታ ገጠም አሰራር እየለሙ ያሉትን እንደ ሩዝ፣ ጤፍ፣ ስንዴ እና ገብስ ያሉ ሰብሎችን ከአረምና ተባይ ነፃ ለማድረግ ጥረት እየተደረገ ነው። ሙሉ የግብርና ፓኬጅ፣ የተሻሻሉ ቴክኖሎጂዎችና የአፈር ለምነት ማሻሻያዎች በጥቅም ላይ በመዋላቸው ሰብሉ በጥሩ ሁኔታ ላይ እንደሚገኝና የታቀደው ምርት እንደሚገኝ ተናግረዋል።
የዞኑ አርሶ አደሮች በበኩላቸው፤ በባለሙያዎች ምክረ-ሃሳብ ታግዘው ማሳቸውን በየዕለቱ በመቃኘትና በማረም ላይ እንደሚገኙ ገልጸው፣ የኩታ ገጠም አሰራርና ዘመናዊ ግብዓቶችን መጠቀም ከቤተሰብ ፍጆታ የተረፈ ምርት ለገበያ ለማቅረብ እንዳስቻላቸው ገልጸዋል።