ቀጥታ፡

ቶተንሃም ሆትስፐርስ ባለማሸነፍ ጉዞው ቀጥሏል

አዲስ አበባ፤ መስከረም 2/2019 (ኢዜአ):-በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የአራተኛ ሳምንት መርሐ ግብር ቶተንሃም ሆትስፐርስ እና ኤቨርተን ያለ ግብ አቻ ተለያይተዋል።

ጨዋታው ማምሻውን በቶተንሃም ሆትስፐርስ ስታዲየም ተከናውኗል።

ባለሜዳው ቶተንሃም የኳስ ቁጥጥር ብልጫን ቢወስድም ግብ ማስቆጠር ተስኖታል።

ተጋጣሚው ኤቨርተን የተሻሉ የግብ እድሎችን መፍጠር ችሏል።

በክረምቱ የተጫዋቾች የዝውውር መስኮት 334 ሚሊዮን ፓውንድ ያወጣው ቶተንሃም በአራት የሊግ ጨዋታዎች ግብ ማስቆጠር አልቻለም። በሁለት ነጥብ 17ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።

ኤቨርተን በስድስት ነጥብ ሰባተኛ ደረጃን ይዟል።

ምሽት አራት ሰዓት ላይ ሰንደርላንድ ከአርሰናል በስታዲየም ኦፍ ላይት የሚያደርጉት ጨዋታ ተጠባቂ ነው።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም