በካፍ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ ወደ ቀጣዩ ዙር አለፈ - ኢዜአ አማርኛ
በካፍ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ ወደ ቀጣዩ ዙር አለፈ
አዲስ አበባ፤ መስከረም 2/2019 (ኢዜአ):- በካፍ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ የመጀመሪያ ቅድመ ማጣሪያ የመልስ ጨዋታ ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ የሱዳኑን ሂላል አል-ሳሂልን 2 ለ 1 አሸንፏል።
በድሬዳዋ ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ ካርሎስ ዳምጠው በ50ኛው እና በ56ኛው ደቂቃ ግቦቹን አስቆጥሯል።
ኢንሳ ሰኢድ ለሂላል አል-ሳሂል ጎሉን ከመረብ ላይ አሳርፏል።
ሁለቱ ቡድኖች በድምር ውጤት ሶስት አቻ መሆናቸውን ተከትሎ ጨዋታው ወደ መለያ ምት አምርቷል።
በዚህም ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ በመለያ ምት 4 ለ 1 በማሸነፍ ወደ ሁለተኛ ዙር ማጣሪያ አልፏል።
ወልዋሎ በሁለተኛው ዙር ከዛንዚባሩ ኬኤምኬኤም እና ከሊቢያው አል አህሊ ትሪፖሊ አሸናፊ ጋር ይጫወታል።
አል አህሊ ትሪፖሊ በመጀመሪያው ጨዋታ 3 ለ 0 ያሸነፈ ሲሆን የመልሱ ጨዋታ ዛሬ ምሽት ሁለት ሰዓት ላይ ይደረጋል።
ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ በአህጉራዊ መድረክ ሲሳተፍ የአሁኑ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው።
የውድድሩ ተሳትፎውን ያረጋገጠው የኢትዮጵያ ዋንጫ ማሸነፉን ተከትሎ ነው።