ቀጥታ፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከአቡ ዳቢ አልጋ ወራሽ ከልዑል ሼህ ኻሊድ ቢን ሙሀመድ ቢን ዛይድ አል ናህያን ጋር መከሩ

አዲስ አበባ፤ መስከረም 2/2019 (ኢዜአ)፦ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከ18ኛው የብሪክስ ጉባኤ ጎን ለጎን፣ ከአቡ ዳቢ አልጋ ወራሽ ከልዑል ሼህ ኻሊድ ቢን ሙሀመድ ቢን ዛይድ አል ናህያን ጋር መምከራቸውን አስታውቀዋል።

‎በቆይታቸውም በዋና ዋና የብሪክስ ቅድመ-አጀንዳዎች እና በኢትዮጵያና በተባበሩት አረብ ኤምሬቶች መካከል ያለውን ሁለገብ ትብብር የበለጠ በሚያጠናክሩ ሂደቶች ዙሪያ ፍሬያማ ውይይት ማድረጋቸውን ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም