ቀጥታ፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከኢራኑ ፕሬዚዳንት መስዑድ ፔዜሽኪያን ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፤ መስከረም 2/2019 (ኢዜአ)፦ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በብሪክስ ፕላስ የቤተሰብ መድረክ ማዕቀፍ ውስጥ፣ ከኢራኑ ፕሬዚዳንት መስዑድ ፔዜሽኪያን ጋር መወያየታቸውን አስታውቀዋል። 

‎ከጉባኤው ጎን ለጎን ያደረጉት ውይይት በቀይ ባሕር አካባቢ ባሉ ወቅታዊ ሁነቶች እና አጠቃላይ በቀጣናው የደኅንነት ሁኔታ ላይ ያተኮረ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ገልጸዋል፡፡

እንዲሁም የውይይትን አስፈላጊነት እና የቀጣናውን መረጋጋት እውን ማድረግ በሚቻልባቸው ጉዳዮች ዙሪያም መክረናል ብለዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም