ቀጥታ፡

ታዋቂው ታይም መጽሔት ስለ ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ባስነበበው ሰፊ ዘገባው ምን አለ?

✍️በታዋቂው ታይም መጽሔት (TIME Magazine) ላይ እንግሊዛዊው ጸሐፊ ጆሽ ዊልሰን “THE POWER TO UNITE AFRICA” (አፍሪካን የማስተሳሰር ኃይል) በሚል ርዕስ ስለ ግድቡ የተነሱት ዋና ዋና ነጥቦች፡-

✍️የአፍሪካውያን ራስን መቻል ማሳያ፡ ግድቡ ከውጭ አበዳሪዎችና ዓለም አቀፍ የፋይናንስ ተቋማት ድጋፍ ውጪ በኢትዮጵያውያን የገንዘብ አቅምና በቦንድ ግዢ ብቻ መገንባቱ፣

✍️አፍሪካውያን የራሳቸውን ልማት በራሳቸው አቅም ማሳካት እንደሚችሉ ያረጋገጠ ታሪካዊ ፕሮጀክት መሆኑን

✍️ቀጣናዊ የኢኮኖሚና የኃይል ትስስር፡ከ5 ሺህ ሜጋ ዋት በላይ የማመንጨት አቅም ያለው ይህ ግድብ፣ የኢትዮጵያን የኤሌክትሪክ ፍላጎት ከማሟላት ባለፈ የኃይል አቅርቦትን ለጎረቤት ሀገራት ተደራሽ በማድረግ የምሥራቅ አፍሪካን የኢነርጂ ገበያ በከፍተኛ ደረጃ እንደሚያስተሳስር

✍️ታላቁ የህዳሴ ግድብ ግዙፍ የልማትና የትብብር ዕድል ከፋችና ቀጣናዊ የጋራ ብልጽግና ማዕከል መሆኑን

✍️ለታችኛው ተፋሰስ ሀገራት ያለው ጠቀሜታ፡የግድቡ የውሃ ፍሰት አስተዳደር የታችኛው ተፋሰስ ሀገራትን የውሃ ፍላጎት የሚያሟላ

✍️ለንጹህ አየር እና አካባቢ ጥበቃ፡ፕሮጀክቱ ንጹህ ኢነርጂን ለቀጣናው ሀገራት በማቅረብ የካርቦን ልቀትን ለመቀነስ እና የአካባቢ ጥበቃ ሥራዎችን ለማጠናከር ቁልፍ ሚና መጫወቱ

✍️ለአፍሪካ ነፃ የንግድ ቀጣና ያለው ሚና፡አፍሪካ በመልክዓ ምድራዊ ወሰኖች ሳትታጠር በኢኮኖሚና በመሠረተ ልማት እንድትተሳሰር ለታለመው የአፍሪካ ነፃ የንግድ ቀጣና (AfCFTA) እውን መሆን እንዲህ ያሉ ግዙፍ ፕሮጀክቶች ወሳኝ መሆናቸውን

✍️ የአፍሪካ ትንሳኤ እና አንድነት ዓርማ፡ የፕሮጀክቱ ጅማሮና ሂደት ዜጎች በልማት ላይ ያላቸውን ቀጥተኛ ባለቤትነት በመላው አፍሪካ እንዲስፋፋ ትምህርት የሚሰጥ ስለመሆኑ

✍️ግድቡ የአፍሪካ ልማት፣የሕዝቦች ትስስር ቋሚ ድልድይና የራስ መተማመን መንፈስ ዓርማ ሆኖ እንደሚቀጥል በዘገባው ዳስሷል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም