ቀጥታ፡

ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን አዲስ ዓመትን በሚኖሩባቸው አገራት በድምቀት አከበሩ

አዲስ አበባ፤ መስከረም 1/ 2019 (ኢዜአ)፦በተለያዩ የዓለም ክፍሎች የሚገኙ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን የ2019 ዓ.ም አዲስ ዓመትን አክብረዋል።

በዓሉ በአገር ውስጥ ብቻ ሳይሆን፣ በዓለም ዙሪያ በሚገኙ የኢትዮጵያ ኤምባሲዎችና ቆንስላ ጽሕፈት ቤቶች የውጭ ሀገራት ዲፕሎማቶችና የዳያስፖራው ማኅበረሰብ በተገኙበት በልዩ ልዩ ባህላዊ ሁነቶች ተከብሯል።


 

የዳያስፖራው ማኅበረሰብ በአዲስ ዓመት አከባበር ላይ ለሀገሩ ልማት እና እጅግ ጠቃሚ ዕድገት የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጿል።


 

አሜሪካ፣ ሩሲያ፣ ቤልጅየም፣ እንግሊዝ፣ ብራዚል፣ ኩዌት፣ ሳዑዲ አረቢያ፣ የተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች፣ ህንድ፣ ፓኪስታን፣ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ፣ ዩጋንዳ፣ ደቡብ ሱዳን፣ ሩዋንዳ እና ጅቡቲ በዓሉ ከተከበረባቸው አገራት መካከል ይገኙባቸዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም